ማቃጠሩን ትተን...
--
ተረት እናስቀድም:-
እማሆይ የአብነት ተማሪዎች ጎጆ በእንግድነት አድረው ሌሊት መቁጠሪያቸውን እየቆጠሩ “አምላክ ሆይ እንደነዚህ ሰነፍ ተማሪዎች ስላላደረከኝ አመሰግንሀለሁ” ሲሉ አንዱ ተማሪ ተነስቶ “እማሆይ ማቃጠሩን ትተው ስለራስዎ ይጸልዩ” አላቸው፡፡
--
ጉዳያችን:-
የእግዚአብሔር መጋቢነት ኃጥእ ጻድቅ አይልም። መጋቢነቱን በዚህ ምድር በሚያጋጥሙን ፈተናዎችና ዕድሎች ለመለካት መሞከር መዳረሻው የብልፅግና ወንጌል እንዳይሆን ያሰጋል። ለቅጣት መቅሠፍት ቢያመጣ እንኳ ለየትኛው ጥፋት እንደሆነ አናውቅም። ምንና ለምን ሠራህ የሚለው የለም።
--
ደግሞስ የማያበራ ጦርነት፣ ረኀብና ርዕደ መሬት ላይ ያለ ሕዝብ የሌላውን መከራ የኃጢአት ውጤት አስመስሎ ጣት ለመቀሰር፣ የሎስ አንጀለስን በደል ለመዘርዘር ምን አንደበት አለው?!
--
ማቃጠሩን ትተን ለራሳችን እንጸልይ!
(በአማን ነጸረ )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ