💒እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን! ጥር 7⃣ በዚህች ቀን ቅድስት ሥላሴ ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው እና ቅዳሴ ቤታቸው ይታሰባል።
****
ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር፤ከናምሩድ ክፋት በኋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ፤ ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በኋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው ‹‹ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ፣ በዚያውም አባቶቻችንን በውኃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው›› ተባባሉ፤ ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ፤ ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል፤ ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል፤መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል፤ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው፤ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ በጠፋን ነበር፤ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና፤ይልቁንም ‹‹ኑ እንውረድ ቋንቋቸው እንደባልቀው›› አሉ እንጂ፤በመሆኑም ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቋንቋዎች ተፈጠሩ፤ እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ፤ ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ አድርገው በተኑት፤ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው ‹‹ባቢሎን›› ሲባል ይኖራል። ዛሬም በክፋታችን ምክንያት ተደበላልቀናል አንድነቱን ያምጣልን ። ሁለተኛው ቅዳሴ ቤታቸው። እነዚህን በማሰብ የዛሬውን ቀን እናከብራለን።
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን❤️✝