♥♥♥ እናትኽ በደስታ ተመልታለች፣ ዮሴፍም በደስታ ተመልቷል፤ አንተም በደስታ የተመላኽ ነኽ፤ የፋሲካ ደስታ ጠቦት የኾንኽ ሆይ! (፩ኛ ቆሮ ፭፥፯) አንተን የወለደች ማርያም አንተን ስትስምኽ ደስ ይላታል! ቀበሮ ሰነፍ ንጉሥ የነበረው ሄሮድስ በድምፁ የሚርበተበትበት የአንበሳ ደቦል ነኽ (ዘፍ ፵፱፥፱፤ ማቴ ፪፥፫) አገዛዙን አበቃኽለት በርሱ ቁጥጥር ሥር የነበረው የራስኽን አገዛዝ ተረከብኽ (ማቴ ፪፥፳)፤ አንተ ንጉሥና የነገሥታት ኹሉ ንጉሥ ነኽ (ራእ ፲፯፥፲፬)፡፡
♥♥♥ አዳምን ከዐቧራ ፈጥረኸዋል (ዘፍ ፪፥፯) የራስኽንም እናት ፈጥረኻል (ሉቃ ፩፥፴፰)፤ ቀዳማዊ ልደትኽ ከአብ የኾንኽ የአንተ ፈቃድ የአንተን ኲለንታ ትስብዕት ቀረጸ፤ የራስኽን መለኮታዊ አኗኗር ሊታወቅ አይቻልም አንተ መዠመሪያ የለኽምና (ዮሐ ፩፥፩)፤ አንተ ስለፈቀድኽ ራስኽን በማርያም ውስጥ አኖርኽ፡፡
♥♥♥ እዚያም እናትኽ፣ ምርጥኽ፣ የእጅኽ ሥራ አገልጋይኽ ማርያም ተንበርክካ አንተን ወልዳለች (ሉቃ ፪፥፯)፤ አንተም ስትወልድኽ፣ ዕቅፍ አድርጋ ስትስምኽ በምስጋናና በጸሎት ታመሰግንኻለች አንተን ስታቅፍኽ ወተቷን ታጠባኻለች ለአንተ በመዘመርና በሕፃንነትኽ መንገድ ፈገግ በማለት፣ አንተ ወተቷን እየጠባኽ በደስታ ስትመላ፣ አንተን የወለደችኽ ለአንተ ወተት ያጠባችኽ በአድናቆት ትዋጣለች፤ አንተ የፈጠርኻት እጅግ ተደምማለች።
♥♥♥ ወልድ ሆይ በአንተም አማካይነት የእናትኽ አእምሮ ይረፍ፤ የእናቱ አስተማሪ፣ የእናቱ አምላክ፣ የእናቱ ጌታ፣ ከእናቱ ወጣትም አዛውንትም የኾነ፣ እስከአኹንም ድረስ በአድናቆት የመላኸኝ አንተ ነኽ (ሉቃ ፪፥፲፱)፤ የአንተ ዕውቀት ያስጨንቀኛል፤ በአንተ ላይ ዐይኑን ሊያሳርፍና በአንተ መዐዛ ሊተነፍስ የማይችል ማን አለ? ድክ ድክ ስትል ተመልካቾች ኹሉ ይደነቃሉ (ሉቃ ፪፥፵፮-፶፩)።
♥♥♥ እናም የአንተ አገላለጽ ኹናቴ ዐዋቂዎችን ፍጥረታትን ያስገርማል፤ ታስገርማለኽም፣ ታናናሾች እጆችኽ ያጨበጭባሉ፣ እግሮችም ይመታሉ፤ በማንኛውም መንገድ እንዴት ተፈቃሪ ነኽ፤ የአንደበትኽ ጒርምርምታ እንኳን ስለአባትኽ ይናገራል (ሉቃ ፪፥፵፱)፡፡
♥♥♥ ውበትኽ ምን ያኽል ታላቅ ነው (መዝ ፵፬፥፪)፤ ብላቴና የኾንኸው እግዚአብሔር ሆይ፣ አፍኽ እንደ ማር ወለላ በጣም ጣፋጭ ነው! ከአፍኽ የሚወጣው ኀይል የሰማያት አካላት እንዲርበደዱ ያደርጋል፤ በአንተ አንድ ድምፅ ይኽ ኹሉ ፍጥረት እንዴት ይሸበራል ብላ ማርያም ተደንቃ ትቆማለች (ሉቃ ፪፥፲፲፱)፤ አንተ በአንተ ጸጋ (ቸርነትን) ለኹለቱም ዓለማት የምትሰጥ ስትኾን ግን በዚኽ ላይ ከፈጠርካት እናትኽ ወተቷን ትጠባለኽ፡፡
♥♥♥ ያንተን ልደት በመዝሙር እንድናገር ላበቃኸኝ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ምስጋና ይግባኽ፤ ለእኔ ጒድለት ራራ ይቅር በል፤ ለአንተ ለጌታዬ ምስጋና ላቀርብና ላመስግንኽ ምክንያቱም ከአንተ ስጦታ የተነሣ ምስጋናኽን እዘምራለኊ፤ በተወለድኽበት ቀን ኀጢአታችንን ይቅር በል፣ እናም በቸርነትኽ ለተበላሸው ሕይወታችን ፈውስን አምጣልን፤ ሰላም ይኹን ጌታዬ፤ በሕዝብኽና በቤተ ክርስቲያንኽ ላይ ግዛ፤ በጣም ክቡር የባሕርይ አምላክ ለኾንኸው አምላክ በአንተ የበዓል ቀን ጌታ ምስጋና ይግባኽ!)” ይላል ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
[ሙሉውን ከነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፌ አንብቡ]
♥እናንተም ዘምሩ አመስግኑ ድንቅ ስለኾነው የአምላክ ልደት♥