Репост из: Hakim
ብርሃን አይቅበሩ ፤ በብሌን ችግር ምክንያት ለአይነ ስዉርነት የተዳረጉ ወገኖች ብርሃን እንዲያገኙ ምክንያት ይሁኑ!" በሚል መሪ ቃል የዓይን ብሌን ልገሣ ወር ይከበራል።
በዓሉ በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚከበር የገለፁት የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው፤ የበዓሉ ዓላማ የተለያዩ የንቅናቄ ሁነቶችን በህዳር ወር ውስጥ በማዘጋጀት ስለዓይን ብሌን ችግሮች፣ ችግሮቹ ስለ ሚያስከትሉት የአይነ ስውርነት ጉዳት ፣ እና ማህበራዊ ጫናዎች፣ ስለ ዓይን ብሌን ህመሞችና ህክምናቸዉ፣ የአይን ብሌን ልገሳ ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች እና እምነቶች፣ እንዲሁም ስለ አይን ብሌን ልገሳ ሂደት ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር ይከበራል ብለዋል።
የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ በበኩላቸው ቀደም ሲል በተደረጉ ጥናቶች በሃገራችን ከ300ሺህ በላይ የብሌን ጠባሳ ዓይነ ስውራን እንዳሉ የተናገሩ ሲሆን ፤ እነዚህ ወገኖች ብርሃን እንዲያገኙ ለማስቻል የአይን ባንኩ በትኩረት እየሰራ መኖሩን እና ከቀደመው ጊዜ ብዙ መሻሻሎች መታየታቸውን ሆኖም የልገሳ ባህሉን ለማጎልበት ርብርብ እንደሚፈልግ አስረድተዋል።
ዶ/ር አምሣለ ጌታቸው የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት የዓይን ባንክ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፤ ስለዓይን ብሌን ችግሮች መነሻ ምክንያትና የመከላከያ መንገዶች ፤ የዓይን ብሌንአሰባሰብ መንዶች እና የዓይን ባንክ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ገለፃ አድርገዋል። ማንኛውም ሰው የአይን ብሌን ለጋሽ ነው ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚዋ ከህልፈት በሃላ በሚደረግ የአይን ብሌንልገሣ ሙሉ የአይን ክፍል እንደማይነሣ፡ የለጋሹን የፊት ገፅታ እንደማይቀይር፤ የአይን ብሌን ልገሣ የእድሜ ገደብ እንደሌለውና የልገሣ ሂደቱም አጭር በመሆኑ የቀብር ሥርዓትንእንደ ማያስተጉዋጉል ወዘተ የሚሉ መሠረታዊ የዓይን ብሌን ልገሣ እዉነታዎችን አብራርተዋል።
በእለቱም የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው ፤ የደምና ሕብረ ህዋስ ባንኩ አምባሣደር አርቲስት ይገረም ደጀኔ ፤ የሶል ጅም የቴኳንዶ አባላትን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች ከህልፈት በሃላ ለሚደረግየአይን ብሌን ልገሣ ቃል የመግባትና የፊርማ ማኖር ሥነ ሥርዓት የተካሄደ ሲሆን የዓይን ባንክ መስራች የሆኑት ዶ/ር ወንዱ አለማየሁ ወንድም በተከበሩ አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የተጻፈ ለአይንባንኩ ድጋፍ የሚውል ብዛቱ 1400 (አንድ ሽህ አራትመቶ) መፅሀፎች በወንድማቸው ዶ/ር ግርማ አለማየሁ በኩል ለደምና ህብረህዋስ ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬሃክተር ወ/ሮ ጤናዬ ደምሴ አስረክበዋል።
መፅሀፉ ለዓይን ባንኩ ማጠናከሪያ እንድውል ታስቦ በስጦታ እንደተበረከተ የገለፁትዶ/ር ግርማ ሁሉም ሰው የዓይን ባንኩን በመደገፍ የወገኖችን ብርሃን የመመለስ ስራ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።
@HakimEthio