👉“ ከራሴ ጋር የማደርገውን እጠላዋለው”👈
👤A4P እንግዳ:- “አስራ ስድስት አመቴ ነው ። የሴት ጓደኛ የለኝም ትክክለኛ ጊዜው ነው ብዬም አላስብም።ነገር ግን ብጥብጥ የሚያደርገኝ የሆነ ጠንካራ ወሲባዊ ስሜት አለኝ።
#ማድረግ #የማልፈልገውን #ነገር #እንዳደርግ #ያደርገኛል። በእግዚኣብሄር አምናለው በቤተክርስቲያንም እሳተፋለው። ላወራቸው የምችላቸው ጥሩ ጓደኞችም አሉኝ ሁሉም ግን እንደኔ አይነት ትግል ውስጥ ናቸው።
ቤተሰቦቼ አማኞች እንደመሆናቸውና በቤተክርስቲያን ስላደግኩ ስለውጪው አለም ምንም ኣላውቅም። እግዚኣብሄርንም የእርሱንም ህዝብ እወዳለው ፣ እግዚኣብሄር በሂወቴ አላማ እና እቅድ እንዳለው አውቃለው።
አሁን አሁን ግን በሂወቴ የእግዚኣብሄርን መልካምነት መጠራጠር ጀምሬኣለው።
እግዚኣብሄር በርግጥ ለኔ መልካም ከሆነ ወሲባዊ ስሜቴን ለምን እስከማገባ ድረስ ገታ አላረገውም😟? ሚሲ , በእውነት ሃጢያትን ማድረግ ኣልፈልግም።
#ከራሴ_ጋር_የማደርገውን_እጠላዋለው ፣ ራሴን እጠላለው ፣አንዳንዴ ሁሉም አንዲያበቃ እፈልጋለው። ባለፈው አመት ራሱን ያጠፋውን የክፍሌ ተማሪ ሁሌ ትዝ ይለኛል።
እሱም በኔ ሁኔታ ውስጥ ኣልፎ ይሆን እያልኩ ኣስባለው……..
❓በዚህም ውስጥ እግዚኣብሄር ለኔ መልካም ነው ትያለሽ?
❓በርግጥ ለኔ መልካም ከሆነ ለምንድን ነው በዚህ ውስጥ የማልፈው? …….. አስጠልቶኛል፣ ራሴንም ጠልቻለው ! እርዳታ እሻለሁ
💁A4P፦ ዋው! ይሄ አስራዎቹ ውስጥ እያለው ከምታገልባቸው ሚሊዮን ጥያቄዎች ኣንዱ ነው። ስለዚህ እንዴት እንደሚሰማህ አውቃለው።
በጣም አስፈሪ ነው ኣይደል? 👌እግዚኣብሄር ላንተ መልካም ነው ወይ? መልሴ “ኣዎ ነው።” የሚል ነው ። ምክንያቱም የእግዚኣብሄር ቃል እንደዛ ስለሚል።( መዝ 100፥5, መዝ 136፥1) …….. መልካም መሆን የእርሱ ማንነት ነው።
አዎ እግዚኣብሄር ለኛ መልካም ነው። እናም በሂዎታችን የሚያደርገው ሁሉ ነገር አንድ አጀንዳ ብቻ ነው ያለው እሱም ፍቅር ነው።(መሃልዬ 2፡4)
👉ስለዚህ ለእንደዚህ አይነት ጥያቄ መልስ ስትፈልግ እውነታው ላይ ለመድረስ ከዚህ መነሳት አለብህ ።
አየህ ብዙ ጊዜ ጾታዊ ማንነታችንን ከእኛነታችን ለይተን ለማየት እንሞክራለን እውነታው ግን አብይ የእኛነታችን ተፈጥሮ ነው። ጾታዊ ማንነታችንን ራሱን የቻለ ነገር ሳይሆን የእኛነታችን ግንባታ አካል ነው። እንደውም ጾታዊ ማንነታችንን የስብእናችን ማዕከል ነው ብዬ ነው ማስበው። የእኛነታችን ምሰሶ ነው። 💯
እግዚኣብሄር በርግጥ ለኛ መልካም ከሆነ ለምን ወሲባዊ ስሜታችንን ለምን እስከምናገባ ድረስ ገታ አላረገውም? አግባብ ጥያቄ ነው። እንደዛ አድርጎ ቢሆን ኖሮ ምንም ያልበሰልን እና ሃላፊነት የጎደለን ባሎችና ሚስቶች ፣ኣባቶችና እናቶች እንዲሁም ዜጎች በሆንን ነበር።
አስተውል ✅የአስራዎቹ ዕድሜያችን አግባብ ባልሆኑ ጾታዊ እሴቶች(sexual immoralities ) የምንባክንበት ዕድሜ ሳይሆን በንጽህና መልካም ዘርን የምንዘራበት ጊዜ ሲሆን ከትዳር በኋላ ያለው ጊዜ ደግሞ በአስራዎቹ ዕድሜያችን የዘራነውን የምናጭድበት ነው።
የአስራዎቹ ዕድሜያችንና የ“single” (በእኔ አመልካከት “single” የሚባለው ከ18 ዓመት በላይ ላሉት ነው) ዓመታት እግዚኣብሄር “ምሰሶውን” በ “ፈተና እሳት”🔥🔥 የሚያጠነክርበት ወቅት ነው፣ ስለዚህም ሌሎች ክርስቲያናዊ ባህሪያት ኣብረው ይገነባሉ።
❎በጾታዊ ጉዳይ የተዘበራረቀ ሂዎት ኖሮት ቃሉን የሚጠብቅ ፣ መልካምና የታመነ ወንድም ወይም የተሰጠ ባልና አባት እስካሁን ኣላገኘሁም። የተመሰገነ ደግሞም በሃጥያት የተሞላ ሂወት ሊኖር አይችልም🔑። የውሸት እየኖረ ሰውን ሊያታልል ይችላል። እግዚኣብሄርንና ራሱን ግን ሊያታልል አይችልም።✅ ለሴትም ቢሆን ተመሳሳይ ነው።በተመሳሳይ ጊዜ የተመሰገነ ደግሞም በሃጥያት የተሞላ ሂወት ሊኖራት አይችልም።💯
❓ለምን? ምክንያቱም ጾታዊ ማንነታችን በትዳር ውስጥ ለአንድ ሰው እንድንሰጥ የተሰጠን በዚያም ውስጥ እንድንረካ ነው።(1ኛ ቆሮ 7፥1-3) ከዚህ ከጾታዊ ማንነታችን ጀርባ ያለውን መሰረታዊ ዓላማ ስናውቅ ሃጥያታዊና ራስወዳድ ነገሮች ይገደላሉ።
👉ነገርግን ለዚህ ዓላማ ጀርባችንን ሰጥተን ጾታዊ ማንነታችንን ለራሳችን ደስታ ፍለጋ ካዋልነው ስብዕናችንን እንረብሻለን። ምክንያቱም ከተፈጠርንበት ዓላማ ዉጪ እየሄድን ሰለሆነ።
ለዛም ነው አንዳንድ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ራሳችንን ለማጥፋት የምናስበው ።
👉የተወደድክ ሆይ ፣ እነዚህ በፈተና የተሞሉ ዓመታት መልካም ናቸው ። ምክንያቱም
✨በእግዚኣብሄር መደገፍንና የእርሱን ጥበቃ የምትማርባቸው አመታት ናቸውና። ✨ለጾታዊ ስሜትህ መልስ ሊሆኑ የሚችሉት ሴቶች ወይም ወሲብ እንዳልሆኑ ትረዳለህ። ✨የሚያስፈልግህ አንድና ብቸኛ ነገር ክርስቶስን ማወቅ እንደሆነ ትማራለህ። ✨ፍላጎቶችህን በራስህ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ለእግዚኣብሄር አንዴት ማቅረብ እንዳለብህ ትማራለህ። በዚህም ሂደት ውስጥ ለአንዲት ሴት ብቻ በፍቅር የሚማርክ ልብ ይኖርሃል። ከዚያም ማንንም ሴት በክርስቶሰ እህትህ እንድትሆን በእግዚኣብሄር እንደተፈጠረች ውድ ስጦታ እንጂ እንደ ወሲብ ዕቃ አታይም።
⛔አስተውል፥ ደግነት፣ ሃቀኝነት ፣ ፍትሃዊነት ፣ሁለገባዊነት ፣ጽኑነትና ሌሎችም መልካምና የተመሰገኑ እሴቶች የሆነ ሰው እጁን ጭኖ ሲጸልይልህ አይደለም የሚመጡት። ይልቁንም በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ፣ እንደ እሳት🔥🔥 በሚነደው ጾታዊ ፈተና ውስጥ በድል ማለፍ ስትችል ያኔ ቀስበቀስ በእርግጠኝነት እነዚህን እሴቶች መያዝ ትችላለህ። ግን አስታውስ በቀላሉ አይመጡም ። ሁሉንም ለማግኘት መታገል አለብህ።
እስራኤላውያን ወተትና ማር ወደ ምታፈሰው ምድር እንዴት በትግል እንደገቡ አስታውስ ። ኣዎ እግዚኣብሄር ከእነርሱ ጋር ነበር ቢሆንም ግን መታገል ነበረባቸው።
👉ጾታዊ ፍላጎቶቻችን ለሌሎች የሂወታችን ዘርፎች መሰረት ናቸው። ነገርግን መሰረቱ የሚንቀጥቀጥ ከሆነ ምንም ነገር በላዩ ላይ ሊገነባ አይችልም። እናም መልካም ትዳር እንዲገነባ መሰረቱ እነዚህ እሰቶች መሆን መቻል አለባቸው።
👉ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለብህ ፈተና አንተን ለማጥፋት ሳይሆን እምነትህ ከወርቅ ይልቅ የተፈተነ ይሆን ዘንድ ነው።(1ኛ ጴጥ 1፥7)
🔑🔑ልታደርገው የምትችለው አንድ በጣም ጥሩ ነገር ይህ ነው፦
👉ለዚህ “ጭራቃዊ ” ስሜትህ በሃጥያት የተሞላ መረጃ ይመግበው ዘንድ ለራስህ አትፍቀድለት ። 👉የምታየውንና የምትሰማውን ለይ፣ ከማን ጋር እንደምትውልም ምረጥ። 👉ይህን ፍላጎትህን ከሚመግቡ ነገሮች መሸሽ ብችኛው መጽሃፍቅዱሳዊ መፍትሄ ነው።(1ኛ ቆሮ 6፥18)
አስታውስ ከእግዚኣብሄር ስሞች ኣንዱ “ተዋጊ” የሚል ነው። ተዋጊም ስለሆነ ተስፋቸውን ለመውርስ ከሚታገሉት ጋር ዓላማውን ለመፈጸም ይወዳል።(2ኛ ዜና 16፥9) ስለዚህ መዋጋትህን እስከመጨረሻው እንዳታቆም 👌። ምክንያቱም በመጨረሻ ሚጠብቅህ ድል በመዋጋትህ እንዳትቆጭ የሚያደርግህ ነውና።💯💯
#single #General
ይህን መልዕክት ለሌሎች ያካፍሉ
💢💢
@PurityTube 💢💢
💢💢
@PurityTube 💢💢