🎯 የደራሲ ብርሃኑ በላቸው "ክቡር ልጆች" መጽሐፍ ሊመረቅ ነው
🎯 ከ"ክቡር ልጆች" መጽሐፍ የተወሰደ ...
"በልጅነት የሚፈጠር የስሜት ጠባሳ ( Adverse Childhood Experiences) እንደጥላ ይከተላል፡፡ ይህ የስሜት ጠባሳ አስፈላጊውን ህክምና ካላገኝ ልጅነትን አልፎ ትዳር ከተመሰረተ በኃላ የስሜት ጠባሳው የመገለጥ ዕድል አለው፡፡ የልጅነት የስሜት ጠባሳ በልጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ አእምሮአዊ፣ ስሜታዊ፣ ማኅበራዊና ጤና ነክ ተፅዕኖዎች ያሳድራል፡፡
አንዲት እናት ልጆቿን ብቻዋን ታሳድጋለች፡፡ የአስተዳደግ ዘይቤዋ ከሌሎች ወላጆች ለየት ይላል፡፡ ልጆቿ ከሰፈር ልጆች ጋር ተቀላቅለው ሲጫወቱ አይቼ አላውቅምና ሁሌም ጥያቄ ይፈጥርብኝ ነበር፡፡ ልጆችሽ ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር ሲጫወቱ አይቼ አላውቅም አልኳት፡፡
“በልጅነቴ ብቸኛ ወንድሜን ያጣሁት ሰፈር ውስጥ በተወረወረ ድንጋይ ነው” ወዲያውም ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
“በጣም አዝናለሁ፤ መጠየቅ አልነበረብኝም” አልኳት
“እነዚህን ብርቅዬ ልጆች እንደ ወንድሜ ማጣት አልፈልግም፡፡ ውጭ እንደ ሌሎች ልጆች ቢጫወቱ ይሞቱብኛል ብዬ እፈራለሁ፡፡” አለችኝ
ህክምና ያላገኘ የልጅነት ጠባሳ ጊዜ ጠብቆ በትዳር ህይወትም ይገለጣል::"
“ክቡር ልጆች” መጽሐፍ በተለያየ ተግዳሮት ውስጥ ለሚገኙ ልጆች የመፍትሄ ሃሳብ ይዞ ቀርቧል፡፡በተለይም ልጆች የሚስተዋልባቸውን የስነ ልቦና ጫና እና የስሜት ስብራት ይተነትናል። መጽሐፉ በጥናት በማስደገፍ የመፍትሄ ሃሳብን በተጨባጭ ያመላክታል፡፡