የአይነት አንድ ስኳር ህክምና አሁናዊ መመሪያዎችና ተስፋ ሰጪ ምርምር ዉጤቶች
የአይነት 1 ስኳር ህመም (type 1 diabetes) ያለበት ልጅ ያላቸው ወላጆች ለልጃቸው ህክምና ተስፋ የሚሰጥ ዜና መፈለግ ያለ ነው። ወላጆች የልጃቸው ህይወት ከኢንሱሊን መርፌ ነፃ እንዲሆን መመኘታቸው ተፈጥሯዊ ነው። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ እነዚህ መሬት ያልያዙ ተስፋዎች አሳሳች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዴም አደገኛ የሆኑ አሳች ዜናዎች የልጅን ህይወት ሊቀጥፉ ይችላሉ።
በዚህ ሳምንት በቲክቶክና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በጣም ሲታይ የነበረ አንድ መረጃ ነበር። ዜናው ‘የአይነት አንድ የስኳር ህመም ስርየት ተገኘለት፣ ከእንግዲህ ኢንሱሊን መርፌ መወጋት እስከወዲያኛው አከተመ እልልልልል አንኳን ደስ አላችሁ’ የሚል ይዘት ያለው የሚያጓጓ ብስራት የያዘ አሳሳች መረጃ ነው። ይህን መረጃ የሰሙ ወላጆች የስኳር ህመም ያለባቸው ልጆቻቸውን ይዘው እኔ ወደምሰራበት የግል ሆስፒታል ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ልጄን ይሄን ህክምና አዝዙልን አሊያም ወደውጭ ሪፈር አርጉን እያሉ ሲጨነቁ ነበር። አሁንም ቅድምም በሚናፈሱ ለታይታ የሚሰራጩ አሉባልታዎች በመታለል ኢንሱሊን ህክምናቸውን በማቋረጥ የሚሞቱትን ወገኖቻችንማ ቤት ይቁጠረው።
ይህ ጽሑፍ ሕይወት አድን የሆነውን የኢንሱሊን ሕክምናን አስፈላጊነት በማጉላት አሁን ያሉ የአይነት 1 ስኳር ህክምና እውነታ፣ ወቅታዊ ተስፋ ሰጭ ግኝቶችና ቀጣይ የምርምር አቅጣጫዎችን ግልጽ ለማድረግ ያለመ ነው።
የዓይነት 1 የስኳር ሕክምና አሁናዊ መመሪያዎች ምን ይላሉ?
የቅርብ ጊዜ የተሻሻሉ የአይነት አንድ ስኳር ህክምና አለም አቀፍ መመሪያዎች እንደሚደነግጉት ኢንሱሊን ውጤታማና አይተኬ አማራጭ ነው። የተሻለ የግሉኮስ ቁጥጥር ለማምጣት እና የስኳር ህመም ተያያዥ የጤና ችግሮችን ለመከላከል አይነተኛ መፍትሄ ኢንሱሊን ነው።
ኢንሱሊን ለአይነት 1 የስኳር ሕክምና የማዕዘን ድንጋይ ነው። ኢንሱሊን እንደዉሃና ኦክስጅን ሁሉ ለሜታቦሊዝም መሳለጥ፣ ለጤናማ እድገትና ሰውነት ግንባታ አስፈልጊ የሆነ ለህልውና ወሳኝ ሆርሞን ነው። ስለሆነም ይህ ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ኢንሱሊንን በተፈጥሮ ማመንጨት ስለማይችሉ መደበኛ የኢንሱሊን መርፌ ወይም የኢንሱሊን ፓምፕ መጠቀም ያስፈልጋቸዋል። የኢንሱሊን ሕክምናን ማቆም በጥቂት ቀናት ለሕይወት አስጊ ይሆናል።
አዳዲስ የአይነት አንድ ስኳር ለማዳን የሚሞከሩ ህክምናዎችና ምርምሮች
1️⃣ የቆሽት ወይም ቤታ ሴል ንቅለ ተከላ (Beta Cell Replacement Therapy: whole pancreas transplantation or Islet Cell Transplantation)
2️⃣ የቆሽት ሕዋስ ማደስ ሕክምና (Beta Cell Regeneration therapy)
3️⃣ የዘረመል አርትዖት (Gene Editing)
ከላይ የጠቀስናቸው በሙከራ ደረጃ ያሉ ህክምናዎች የረጅም ጊዜ ጤና የማሻሻል ትልቅ ተስፋ የሰጡ ሆነዋል።
እነዚህ ተስፋ ሰጪ የሙከራ ደረጃ ሕክምናዎች ገና ጥቅም ላይ ለመዋል ዝግጁ አይደሉም። አበረታች ውጤቶችን ቢያሳዩም ገና በሙከራ ደረጃ ላይ ናቸው። ለሁሉም ታካሚ በሰፊው ከመሰጠታቸው በፊት ብዙ ተጨማሪ ጥብቅ ምርመራ እና ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል።
የጠቀስናቸው እና ሌሎችም የሚያጓጉ ሕክምናዎች እስኪገኙ ድረስ ዓይነት 1 የስኳር ህመምን በኢንሱሊን ማከም ና ስኳርን መቆጣጠር ወሳኝ ነው። እነዚህን ለዉጦች በተስፋ እየተጠባበቅን አሁን ላይ የተረጋገጡ ተጨባጭ ህክምናዎችን በቁርጠኝነት መቀጠል ይገባል። ስለሆነም አሁን ላይ ያሉትን የሚመከሩ የተረጋገጡ ህክምናዎች መቀጠል አስፈላጊ ነው። የኢንሱሊን ህክምና ፍጹም እንከን የለበትም ባይባልም ሕይወት አድን ነው።
የዚህን ጽሁፍ ሙሉ መረጃ በዶ/ር መልኣኩ ታዬ ብሎግ https://melakutaye.com/type-1-diabetes-current-treatment-and-future-hopes/ እንዲያነቡና ለሌሎችም እንዲያጋሩ በትህትና እጋብዛለሁ።
@hakimmelaku