የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጠ።
**********
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥር 7/2017 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫ ሰጥቷል።በዚሁ መሰረት
1.ከደቡብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዲሁም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እጬ ዳኞች ላይ የፌደራሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 81/4 አስተያየት እንዲሰጥበት በተጠየቀው ላይ ከተወያየ በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል፣
2.የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ የሆኑት አቶ ጌታሁን ገ/መስቀል በፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሙስና መከላከያ ዳይሬክቶሬት የጥቆማ ተቀባይ ክፍል ሀላፊ ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥቷል፣
3.በፌደራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ፍ/ቤት ዳኞች ምልመላ ሂደት ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ የሰጠ ሲሆን ለፌደራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት ዳኝነት ለህዝብ አስተያየት የማለፊያ ነጥብ ወስኗል።በዚሁ መሰረት ለሴት እና አካል ጉዳተኞች 68 እና ከዚያ በላይ ለወንዶች 73 እና ከዝያ በላይ ለህዝብ አስተያየት የማለፊያ ነጥብ እንዲሆን ወስኗል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ በውጤቱ ላይ የቀረቡ 4 ቅሬታዎችም ከእጩ ዳኞች ምልመላ መመሪያ አንጻር ከታዩ በኋላ ተቀባይነት የላቸውም በማለት ወስኗል።