የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አስክሬን አዲስ አበባ ገብቷል
*****
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አስክሬን በህክምና ሲረዱ ከቆዩበት ኬንያ ናይሮቢ ምሽቱን አዲስ አበባ ደርሷል፡፡
አስክሬናቸው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የሙያ ባልደረቦቻቸው አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ሐሙስ በአዲስ አበባ እንደሚፈጸም የቀብር አስፈጻሚ አብይ ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ማርቆስ ሌራንጎ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል፡፡
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት የነበሩ በሳል ፖለቲከኛ እና ምስጉን መምህር ነበሩ፡፡