"ጣናን ተንተርሳ የተመሠረተችው ባሕር ዳር ከተማ ቱሪዝም ዋነኛ መወዳደሪያዋ ነው" የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ከፍተኛ መሪዎች የከተማዋን የኮሪደር ልማት፣ የአስፋልት መንገድ ግንባዎች እና ሌሎችንም ልማቶች ነው የተመለከቱት።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ደረጃቸውን የጠበቁ ሰፋፊ የአስፋልት መንገዶች የባሕር ዳር ከተማ መለያዎች ነበሩ፤ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ደግሞ ከተማዋ ውብ ጎዳናዎች እንዲኖሯት የበለጠ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። የተመለከቱት ዘመናዊ የአስፋልት መንገድ ግንባታ በአይነቱ፣ በስፋቱ እና በጥራቱ የተለየ እንደኾነም አንስተዋል።
በጣና ዙሪያ የተገነቡ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችም ሕዝብን ማዕከል ያደረጉ እና ከፍተኛ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ናቸው ብለዋል።
"ቱሪዝም ጣናን ተንተርሳ የተመሠረተችው ባሕር ዳር ከተማ ዋነኛ መወዳደሪያዋ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ ለዘርፉ መስፋፋት የሚያግዙ መዳረሻዎችን በትኩረት ማልማት ግድ እንደሚል አሳስበዋል።
የተሠሩ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እና የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ ሲጠናቀቅ የከተማዋን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።
ባሕር ዳር ከተማ ሰላሟን ከማስጠበቅ በተጨማሪ ለመጭው ትውልድም ጭምር የሚተርፍ የመሠረተ ልማት ሥራ እያከናወነች እንደኾነ ስለመመልከታቸውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በቀጣይ የማኅበረሰቡን ተሳትፎም የበለጠ በማጠናከር ተጨማሪ ልማቶችን መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል። ለዚህ ደግሞ የከተማዋ አመራሮች አሁን ላይ ያሳዩትን የልማት ቁርጠኝነት የበለጠ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ነው ያሉት።
ሚኒስትሩ እየተከናወኑ ያሉት የልማት ሥራዎች ከቱሪዝም በተጨማሪ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉም ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸውም ጠቁመዋል። መንገዶች እና መንገዶችን ተከትሎ የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች አልሚ ባለሃብቶችን የመሳብ አቅማቸው ከፍ ያለ መኾኑን ነው ያነሱት።
አሚኮ