የኢሰመጉ መታገድ የዘገየ ውሳኔ ነው። መታገድ የነበረበት ፋኖ ወደጫካ ሊወጣ ሲያሟሙቅ በታየበት ወቅት ነበር። ኢሰመጉ(ኢህአፓ ሰማያዊ መኢአድ ጎዴፓ) ጫካ ገባው ካለው ጃውሳ የሚለየው ክላሽ ታጥቆ በፎቶ ባለመታየቱ ብቻ ነው። በሌላ መልኩ ኢሰመጉ አሁን ላይ ሕልውና ያለው እናት ፓርቲ ማለት ነው። እናት ፓርቲ ኢሰመጉና ፋኖ አንድም ሶስትም ናቸው። ፋኖ ወደ ጫካ ሲወጣ ኢሰመጉና እናት ፓርቲ የከተማውን ግንባር ሸፍነው ጫካ ወጥቶ ለነበረው ጃውሳም በተቀናጀ መንገድ በመግለጫ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ሲያግዙ የቆዩ የፈነኑ አካላት ናቸው። በየጊዜው መረጃ ስንቅና ትጥቅ በማቀበል የሚችሉትን ሁሉ ድጋፍ ሲሰጡ ቆይተዋል። እስካሁን ያልሰጡት ድጋፍ ቢኖር የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው። እናም የኢሰመጉ መታገድ ዘገየ እንጅ ትክክል ነው። ደግሞ እሱ ያልታገደ ማንስ ይታገዳል? ለውጡን ተከትሎ የፖለቲካ ድርጅት ብቻ ሳይሆን የለየለት የነውጥ የትጥቅ ድርጅት ነው እኮ የሆነውም።