"ነገሩ ወሰብሰብ ያለ ነው!"
መንግስት የደመወዝ ወለል ለማውጣት ዳተኛ መሆኑን ከሰማን ቆይተናል።
የገቢዎች ቢሮ ግን ከደሞዝ የምቀበለውን ግብር የማስከፍለው በራሴ የደሞዝ ተመን ነው ብሏል። ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ማለት እንዲህ ያለውን ሲያዩ ነው።
በዚህ መሠረት ለጽዳት ሠራተኛ የማስከፍለው የወር ደሞዙን በ5000 አስቤ ነው ብሏል። በተግባር የሚታየው ደሞዝ ግን ከዚህ ከግማሽ በታች ነው። ይህ ደሞዝ ትንሽ በመሆኑ የደሞዝ ወለል ይተመንልን ሲል ኢሠማኮ (CETU) ሲጠይቅ መቆየቱን በመሪው በአቶ ካሣሁን ፎሎ በኩል በተደጋጋሚ ሲነግረን ቆይቷል።
የመንግስት የገንዘብ አፒታይት ሰፍቶ የታክስ ጫናው ንግዱን እያወከ ነው። ይህንን "ሃይ" የሚልም ጠፍቷል።
https://t.me/Tamrinmedia