በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮችን ለገበያ አቀረበ
ነሀሴ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) በላይነህ ክንዴ ግሩፕ (ቢኬጂ) ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ቻርጀሮችን ለገበያ አቅርቧል።
በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሠሩ ሚኒባስና የከተማ አውቶብሶችን በሀገር ውስጥ በመገጣጠም ለገበያ ያቀረበው በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ፈጣን የኤሌክትሪክ ቻርጀሮችን ለገበያ ማቅረቡን ዛሬ አስታውቋል።
እነዚህ ፈጣን ቻርጀሮች አንድን መኪና በደቂቃዎች ውስጥ ሙሉ የማድረግ አቅም ያላቸው ናቸው ተብሏል።
በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሣቀሱ ተሽከርካሪዎች ቁጥር በሀገራችን እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ድርጅቱ የኤሌክትሪክ መሙያ ጣቢያዎችን ችግር ለመቅረፍ በርካታ ቻርጀሮችን ለገበያ ማቅረቡን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ጠቁሟል።
በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚንቀሣቀሱ ሚኒባሶችን ዘመናዊና የከተማ አውቶብሶችን በመገጣጠም ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ በመረጃው ተገልጿል።