በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተሰማሩ የ49 ኤጀንሲዎች ባለቤቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ጳጉሜን 1/2016 (አዲስ ዋልታ) በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተሰማሩ የ49 ኤጀንሲዎች ባለቤቶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለአዲስ ዋልታ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን አስመልክቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ወንጀሉን በመፈፀም ላይ የሚገኙ አካላትንና የትስስር ሰንሰለታቸውን ለመለየት ሰፊ ጥናትና ክትትልና ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ጥናቱንና ክትትሉን መነሻ በማድረግ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በተከናወነው ስምሪት በድርጊቱ ሲሳተፉ ተደርሶባቸው የተጠረጠሩ የ49 ኤጀንሲዎች ባለቤቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
እንደ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ፤ መንግሥት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስቀረት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ስምምነቶችን በመፈራረም ዜጎች ጥቅማቸው ሳይጓደልና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ውጭ ለሥራ እንዲሰማሩ የሚያስችል ሕጋዊ አሠራር ዘርግቷል፡፡
ይህን የሥራ ስምሪት የሚመራ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከማቋቋም በተጨማሪ ሕጋዊ ስርዓትን የሚያሳልጥ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ በማድረግ ከ1ሺ ሁለት መቶ ለሚበልጡ ኤጀንሲዎች ፈቃድ ሰጥቷል፡፡
👇👇
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0ZJGNHbFP2zjEp5Cc7eWMdU7EV7LiyTaNaoww4ncJzj9rxHbRQRNTrj6NG5Xeq2b6l