“ሪፎርም ኮርነር” የተሰኘ መጽሐፍ እና የቴሌቪዥን ዝግጅት ይፋ ተደረገ
ጳጉሜን 2/2016 (አዲስ ዋልታ) ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተከናወኑ ሪፎርሞችን የተመለከቱ ጉዳዮች የተዳሰሰበት “ሪፎርም ኮርነር” የተሰኘ መጽሐፍ እንዲሁም ሪፎርሙን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚዳስስ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ዝግጅት በዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
ለንባብ በበቃው መጽሐፍ በኢትዮጵያ በፍትሕ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሲቪል ሰርቪስ ዘርፎች የተገኙ ስኬቶች እና የተደረጉ ማሻሻያዎች ተዳሰዋል።
በተጨማሪም በዛሬው ዕለት “ሪፎርም ኮርነር” የተሰኘ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ዝግጅት በአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ለተመልካቾች መቅርብ ይጀምራል።
የቴሌቪዥን ዝግጅቱ እና መጽሐፉ ለበርካታ ወራት ከፍተኛ ዝግጅት እና ጥናት በማድረግ የተሰራ ነው።
ዝግጅቱን ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን አከናውኗል።