በ2016 ዓ.ም 8 ሺሕ 854 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረዋል - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
ጥቅምት 1/2017 (አዲስ ዋልታ) ባሳለፍነው የ2016 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ተቋማት ላይ 8 ሺሕ 854 የሳይበር ጥቃቶች መሰንዘራቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ አስታወቁ።
ዋና ዳይሬክተሯ ይህንን የገለጹት በ5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የመክፈቻ ስነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
በኢትዮጵያ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ በተለይም የፋይናስ ተቋማት፣ የመከላከያ፣ የጤናና የኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ተቋማት የጥቃቱ ኢላማ መሆናቸውን አመላክተዋል።
በቀጣይ አስር ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ጥቃት ይበልጥ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እንደሚሆን ገልጸው በፈረንጆቹ 2027 ዓለም 23.7 ትሪሊየን ዶላር በዚው ጥቃት ልታጣ እንደምትችል መረጃዎች የሚያሳዩ መሆኑንም አንስተዋል።
👇👇
https://web.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0JxsM1pjYBQMJd136s7d3Y7UeM4fxMbZ1MbT5ARk9jSEnMmY9sumheY5xpCnFfsk5l