#ለመረጃ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ወለድ መጠኖች ላይ ጭማሪ ተደረገ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል።
ይህ ጭማሪ የመጣው መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት አካል እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።
በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፦
የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣
የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣
የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣
የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ጭማሪ አሳይተዋል።
ይሁን እንጂ ለኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ብድሮች የወለድ ምጣኔ በ12 በመቶ እንደነበረው ይቀጥላል ተብሏል።
የውጭ ምንዛሬ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰራተኞች የግል ብድሮች በስምምነቱ ውል ላይ በመመስረት ከ11 በመቶ እስከ 13 በመቶ የሚደርስ ሲሆን፣ ለየት ያለ ከፍተኛ ዋጋ ላላቸው ደንበኞች ሰራተኞች የግል ብድሮች በ12 በመቶ እንደነበረው እንደሚቀጥልም ታውቋል።
ምንጭ :- ካፒታል ጋዜጣ