ስሚኝማ_𝙗𝙡𝙚𝙣𝙚
ልቤ ሄዶ ሄዶ መንገድ ላይ ቢደክምም፤
አቀበቱን አልፎ ሜዳ ላይ ቢወድቅም ፤
በአንቺ ፍቅር ጦስ ጉልበቴ ቢዝልም ፤
ግን እግዜር አምላኩ ላልችል አልሰጠኝም።
ስሚኝማ ውዴ አንድ እውነት ልንገርሽ ፤
ባንቺ ስቃይ ማየት ፈልጎ አይደለም ልቤ ያፈቀረሽ ፤
እንዲ ክንፍ ብዬ ዝልፍልፍ ስልልሽ ፤
እያየሺኝ ብትሄጂ እንኳን አልፈሽ ፤
ስሚኝማ ውዴ አንድ እውነት ልንገርሽ ፤
ልቤ ግን ይኖራል ሁሌ እንዳፈቀረሽ።
አፈቀርንህ ቢሉኝ መቼ ይገባኝና ፤
እያሰብኩሽ አንቺን መልሼ እንደገና ፤
ልቤ ባንቺ ፍቅር ታውሮ ቀረና ፤
አዎ…..........
አፈቀርንህ ቢሉኝ መቼ ይገባኝና ።
መጥፎሽን አልሻም ፈፅሞ እኔ ማየት ፤
የትም ቦታ ብትሆኚ የትም ይሁን የት፤
ያድርግልኝ ሞቴን እግዜር ካንቺ በፊት።
ስሚኝማ ውዴ አንድ ነገር አለ የምነግርሽ፤
ብትሄጂ ካጠገቤ ከኔ ተለይተሽ ፤
እውነትን ተሻግረሽ…..............
ልቤ ግን ይኖራል ሁሌ እንዳፈቀረሽ።
🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗🤗
✍️# 𝙟𝙤𝙮𝙚 😋
#𝕤𝕙𝕒𝕣𝕖
#𝕃𝕚𝕜𝕖