አኹን ላይ በአዲስ አበባ በ4ኪሎ፣ 5ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ቤላ፣ አምባሳደር፣ ፈረንሳይ፣ ቦሌ፣ ካዛንችስ፣ ገርጂ እና በኹሉም ወንዝ አለባቸው በሚባሉ የከተማዋ አካባቢዎችና በሌሎችም አካባቢዎች በዋና ዋና መንገዶች ዳርቻ ከፍተኛ ፈረሳዎች እየተካሄዱ/እንደሚካሄዱ በይፋም ይፋዊ ባልሆነ መንገድም እያየንና እየሰማን ነው። በኑሮ ውድነትና ሰላም እጦት ወገቡ የጎበጠን ማኅበረሰብ አለፍ ሲልም ገሃድ የወጣ የከተማ ውስጥ ረሃብ ባለበት በተጣደፈ አኳኋን እንዲህ ዜጎችን ከድጡ ወደ ማጡ መውሰድ ለምን እንደተፈለገ አፍራሾቹ ብቻ የሚገባቸው እውነት ኾኖ ዋናው ግን ልማት ሳይሆን ነባሩን ማኅበረሰብ ከማኅበራዊ መሠረቱ መነጠልና ማሳሳት፣ የእምነት ቦታዎችን ያለሰው ማስቀረት፣ ሰውን ከመሐል መግፋት ከዳር ማስጨነቅ፣ መንግሥት የገጠመውን በጀት እጥረት ከሊዝ ሽያጭ መሰብሰብ፣ ሥርዓቱን ተጠግተው ፍርፋሪ ለሚጠብቁ "የአየር ባየር ባለሀብቶች" ማበልጸጊያ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ በሌላ በኩል እንደሥርዓት በሀገር ደረጃ ያጣውን ቅቡልነትና ቁጥጥር በማዕከል አለሁ ለማለትና አዲስ የከተማ ትርክት/narration/ ከመፍጠር የመነጨ ለመሆኑ ነጋሪ አይሻም። ቢያንስ ቢያንስ ተነሽዎችን ከአልሚዎቹ/ባለሀብቶች ጋር በመስማማት ከሚሠራው ሕንፃ አንደአቅማቸው የድርሻቸውን አግኝተው እንዲኖሩ ማድረግ በተገባ ነበር፡፡ ስማችን የተጠቀሰው የትብብር ፓርቲዎች እንዲህ ያለውን ኢ ሕገ መንግሥታዊ፣ አግላይ፣ የበላይና የበታች አካሄድ በጽኑ እናወግዛለን፡፡
በመሆኑም፣
1. መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የዜጎች መብት እንዲያከብርና ማኅበረሰቡን መሠረታዊ በሆነ መልኩ ከሚያናጋ በልማት ሽፋን የሚተገበር ደባ እንዲያቆም፤
2. የፈረሳው ሰለባ የሆነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ባገኘው አጋጣሚ ኹሉ ድርጊቱን በሰላማዊ መንገድ በመቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብቱን እንዲያስከብር፤
3. ከቦታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የነበሩበትን ቦታ ካርታና መሰል የነዋሪነት/ባለ ይዞታነት/ ማስረጃዎች በጥንቃቄ እንዲያስቀምጡ፤
4. አዲስ በፈረሱ አካባቢዎች ላይ እየገነባችሁ ያላችሁ ባለሀብቶች የተፈናቀለ ወገናችሁ አንድ ቀን ተመልሶ እንደሚመጣ አድርጋችሁ ማሰብም መሥራትም እንዳለባችሁ እንድታውቁት ለማሳሰብ እንወዳለን።
እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ
መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ