ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
ባለፈው ሳምንት ከኮር በላይ የሆኑ የትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ስብሰባ ማድረጋቸው ይታወቃል። ከስብሰባው በኋላ መግለጫ ያወጡ ሲሆን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከኮር በላይ ተብሎ በቀረበው መግለጫ ላይ ለመወያየት ጥር 16 ቀን 2017 አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን ኣስተላልፏል።
1) በሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦችን ስም የቀረበና የተላለፈው የውሳኔ ሐሳብ ለአንድ ብዱን የወገነ፣ መንግስትን የሚያፈርስ፣ ሰራዊቱን የሚበታትን፣ የፕሪቶሪያ ስምምነትን የሚጥስ እና መሰረታዊ ስሕተት ያለበት በመሆኑ፤ በአስቸኳይ እንዲታረምና ወደ ታችም እንዳይወርድ ተወስነዋል።
ሀ) መግለጫው ከሰራዊቱ ተልዕኮ ያፈነገጠ እና በበርካታ ጉዳዮች ላይ ተቋማዊነትን ያልጠበቀ እንደሆነ በጥልቀት ታይቷል። ሰራዊቱ በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት አንዱን ቡድን በመቃወም ሌላውን ለመደገፍ የሚያስችል ተልእኮ እንደሌለው እየታወቀ “ጉበኤ ያደረገ እና ጉባኤ ያላደረገ” በሚል የተደረገ ውይይት እና ያስተላለፈው ውሳኔ ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው የጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔው አስምሮበታል። ከዚህ ባለፈም እራሱ የፓርቲ እውቅና ሰጪ፣ ስልጣን ሰጪ እና ከልካይ እንደሆነ አድርጎ ያስተላለፈው ውሳኔም ተቀባይነት የሌለው እና ስርዓት አልበኝነትን የሚያነግስ ብቻ ሳይሆን፤ ትግራይን መንግስት አልባ የሚያደርግ፣ የህዝባችንን አንድነት የሚያናጋ እንዲሁም የሰራዊታችንን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነው። እንደ ተቋምም ከኮር በላይ አመራር የሚባል ህጋዊ ኣደረጃጀት የሌለበት በመሆኑ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ሕጋዊ ስልጣን ስልጣን የለውም።
ለ) የወረዳ፣ የከተማ/የክፍላተ ከተማ ምክር ቤቶችን በማስመልከት ያስተላለፈው ውሳኔም በተመሳሳይ መልኩ ከተልዕኮው ውጪ ነው። መዋቅሮችና ተቋማትን የማስተካከል ወይም ሕግ የማውጣት እና የመሻር የመንግስት ሥልጣን ሆኖ ሳለ፤ የአንድ የፖለቲካ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት ተብሎ የተላለፈ ውሳኔ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። ይህ ሆን ተብሎ መንግስት ስራውን እንዳይሰራ የሚያደርግ እና የህዝብንና የሰራዊቱን አንድነት የሚያናጋ ተግባር መሆኑን መላው ህዝባችንና ሰራዊታችን ሊገነዘቡት ይገባል። ይህ እንቅስቃሴ ሆን ተብሎ መንግስትእግር እንዳይተክል የሚያደናቅፍ ተግባር ስለሆነ በአስቸኳይ መታረም አለበት ብሏል ካቢኔው።
2) መንግስትን እንደገና ማዋቀር በተመለከተ የተላለፈው ውሳኔ ደግሞ የአንድ ቡድን ልክ የለሽ የስልጣን ጥማትን ለማርካት ሲባል የፕሪቶሪያ ስምምነትን የሚጻረር፤ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው። ይህ የትግራይን ህዝብ ወደ ሌላ የጦርነት አዙሪት የሚያስገባ ስክነት እና ብስለት የጎደለው ውሳኔ ስለሆነ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሊቀበለውስ ይቅር ለአፍታም ቢሆን ሊያስበው እንደማይችል አፅንኦት ሰጥቶበታል። በመሆኑም ውሳኔው በአስቸኳይ እንዲታረም አቅጣጫ አስቀምጧል።
3) ሁሉንም የጸጥታ መዋቅር ወደ አንድ ማዕከል ለመሰብሰብ የቀረበው ሐሳብም ህገ መንግስታዊ ያልሆነ እና የትግራይን ችግር ይበልጥ የሚያባብስ ነው ብሎታል። አቀናጅቶ ማሰማራት አይቻልም ባይባልም በአንድ ቋት ውስጥ ካልገቡ የሚለው ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም። ይሁን እንጂ ሁሉም የፀጥታ አካላት ሙያዊ ነፃነታቸውንና ሕጋዊ ኃላፊነታቸውን በመጠበቅ በቅንጅት እንዲሰሩ ለማድረግ በቀጣይነት የሚሰራበታል ይሆናል።
4) በዚህ መልኩ የቀረቡት ውሳኔዎች መሰረታዊ ስሕተቶች ያለባቸው እና ተፈጻሚነት የሌላቸው መሆናቸውን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አስታውቋል። ውሳኔዎችን ለማፍጠን ወደ ታች ለማውረድ የተደረገው ጥድፊያም በአስቸኳይ እንዲቆምና በትክክለኛ መርህ ላይ የቆሙ እና ይህን የተሳሳተ ውሳኔ የተቃወሙ የሰራዊት አመራሮች ላይ የሚተላለፍ ምንም አይነት ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆንም ካቢኔው ወስኗል።
የተከበርክ በሃገር ውስጥም በውጭም ያላህ የትግራይ ህዝብ፦
በትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ስም የወጣው መግለጫ እጅግ እንዳሳዘነህና እንዳሳሰበህ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በጥልቅ ተረድቷል። በሰራዊቱ የአመራር ስህተት ዳግም ወደ ጦርነት እንዳትገባ በጣም እንዳሳሰበህም በውል እንገነዘባለን። ሁኔታው እጅግ አሳዛኝና አሳሳቢ ቢሆንም፣የጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔው አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ውሳኔዎቹ እንዳየተገበሩ ወስኗል። በአካባቢያችሁ ያሉትን እንቅስቃሴዎች በቅርበት እንድትከታተሉ እና ስህተቶች ከተከሰቱም ቶሎ እንዲታረሙ በጥብቅ እናሳስባለን። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰላማችሁን እንትጠብቁ እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን የሚጥስ እና ወደ ጦርነት የሚመልሰን ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ በጥብቅ እንድትቃወሙ እናስገነዝባለን።
የተከበርክ የትግራይ ወጣት፦
በዚህ ሳምንት በተላለፉ የትግራይ ሰራዊት አመራር ውሳኔዎች ምክንያት በጣም እንደተገረማችሁ ይገባናል። ተስፋ ያደረጋችሁበት የለውጥ መንገድ እንዳይደናቀፍ እና ተሳትፎአችሁ እንዳይመክን ያሰደረባችሁ ስጋትም በውል እንገነዘባለን። የትግራይ ህዝብ እንደገና የአንድን ቡድን የስልጣን ጥማትን ለማርካት ተብሎ ወደለየለት ጦርነት እንዳይገባም ስጋት ገብቷችኋል። የጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔው ከሰራዊቱ ተልዕኮ ውጪ የተላለፈው ውሳኔ በዝርዝር ተመልክቶ ተግባራዊ እንዳይሆን እና ወደ ታችም እንዳይወርድ መወሰኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። እናንተም የተሳሳቱ ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዳይሆኑ ከሕዝባችሁና ከሠራዊታችሁ ጋር በመሆን በርትታችሁ መታገል አለባችሁ። ከምንም ነገር በላይ ደግሞ ሰላማችሁን እንድትጠብቁ እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጎን በመቆም ዳግም ጦርነት ሊያሰነሱ የሚችሉ መንገዶችን እንድትዘጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የተከበራችሁ የትግራይ የፀጥታ ኃይሎች
በዚህ ሳምንት በተላለፉ ተገቢ ያልሆኑ ውሳኔዎች እንዳዘናችሁ እና የራሳችሁ ህልውና አደጋ ላይ እንዳይወድቅ እና ትግላችን ሙሉ በሙሉ እንዳይደናቀፍ ከፍተኛ የሆነ ስጋት እንዳደረባችሁ ግልፅ ነው። በአስደናቂ ጀብዳችሁ ያስጠብቃችሁት ሰላም እንዳይደፈርስ፣ በከፈላችሁት መስዋዕትነት ያቋቋማችሁት ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳይፈርስ እና ህዝባችሁ ወደ ሌላ ዙር ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዳይገባ በእጅጉ እንዳሳሰባችሁም ከልብ እንረዳለን። ከምንም ነገር በላይ ደግሞ የከፈላችሁት መስዋዕትነት፣ የአካል ጉዳት እና ትግላችሁ አደጋ ላይ ወድቆ የአንድ ቡድን መሣሪያዎቸእ እንደሆናችሁ ተደርጎ የቀረበው ሐሳብ በጣም እንዳሳዘናችሁ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ተረድቷል። መግለጫው በጥልቀት ብመመርመርም ተቀባይነት የሌለው እና በምንም መልኩ ተግባራዊ እንደማይሆንም ወስነናል። እናንተም እነዚህ ውሳኔዎች በማንኘኣውም መልኩ ተግባራዊ እንዳይሆኑ ጠንክረችሁ እንድትታገሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
መልእክት ለኢትዮጵያ መንግስት