በዚህ ሳምንት በከፍተኛ የሰራዊት አዛዦችን ስም የተሰጠው መግለጫ የትግራይ ሰራዊት ወይም ጊዜያዊ አስተዳደር አስተያየት እና ውሳኔ አይደለም። የትግራይ የፀጥታ ኃይል፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ እና የትግራይ ህዝብ ፍላጎት በሰላማዊ መንገድ በመታገል የፕሪቶሪያ ስምምነትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግ በተለያዩ ኃይሎች ሥር ሆኖ እየተሰቃየ ያለው ህዝባችን ነፃ ማውጣት፣ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ፣ ሕገ መንገስታዊ የትግራይ ወሰን ወደነበረበት እንዲመለስ ማድርግ ነው። ይህ በከፍተኛ የጦር አዛዦች ስምየ ወጣው መግለጫም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ በጥልቀት ተመርምሮ ውድቅ ተደርጓል። የፌደራል መንግስትም እንደኢሁ የፕሪቶሪያ ስምምነት በትክክል ተፈፃሚ እንዲሆን እና የሰላም ሂደቱን ዋስትና አስተማማኝ በማድረግ በተለያዩ ኃይሎች እየተሰቃየ ያለው ህዝባችን ነፃ እንዲወጣ፣ በግፍ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ፣ የትግራይ ሕገ-መንግስታዊ ወሰን እንዲከበር፤ በአጠቃላይ የፕሪቶሪያ ስምምነት በአግባቡ እንዲፈፀም የተሟላ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
መልእክት ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ
የትግራይ ህዝብና ጊዜያዊ አስተዳደር ፍላጎትና ምኞት ሰላም ነው። ለዚህም ነው በፕሪቶሪያ ስምምነት አተገባበር ላይ በርካታ ችግሮችና ፈተናዎች ቢያጋጥሙንም ጥያቄዎቻችንን በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለመፍታት ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርበን እየሰራን ያለነው። አሁን ግን በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ እጅግ የከፋ ከመሆኑ የተነሳ ሁኔታው ከቁጥጥራችን ውጭ ሊወጣ ይችላል። ስለሆነም የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የተሟላ ድጋፍ እንዲታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በዚህ ሳምንት በከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ስም የወጣው መግለጫ የትግራይ ሰራዊትም ሆነ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የማይወክል ውሳኔ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማረጋገጥ እንሻለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን እና የትግራይን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ግዴታችሁን እንዲትወጡ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ
ጥሪ ቀን 20