#ሀገረ_ምስካይ(የመማጸኛ ከተማ)
በኦሪት መጻሕፍት ላይ የሰፈረ ለእሥራኤላውያን የተሰጠ አንድ ልዩ ሀገር አለ እርሱም የመማጸኛ ሀገር "ሀገረ ምስካይ" ይባል ነበር።ሀገረ ምስካይ(የመማጸኛ ሀገር) ማለትም ሰው ለወፍ ለዛፍ ብሎ ድንጋይ ወርውሮ አንድም ባለማወቅ ነፍስ የገደለ እንደ ኾነ ያለ ፍርድ ባለማወቅ በሠራዊቱ በዳኛው ፊት ቆሞ እውነቱ እስኪመረመር ድረስ እንዳይሞት(እንዳይገደል) ይማጸንበት ዘንድ የሚጠጋበት አገር ማለት ነው።
በዮርዳኖስ ሦስት አገሮች በከነዓን ሦስት ሀገሮች በጠቅላላ ስድስት ሀገሮችን ለይተዉ ለመማጸኛ እና ለስደተኛ እንዲሰጡ በእስራኤላውያን ዘንድ ሕግ ነበር። ከእነዚህም ለነገደ ሮቤል መማጸኛ ባሶር ለነገደ ጋድ መማጸኛ አራሞት ለነገደ ምናሴ መማጸኛ ባሳን እንዲኾኑ ተለይተዉ ተሰጥተዋል፡፡
ሙሉ ቃሉ:-
"በስሕተት ነፍስ የገደለ ወደዚያ ይሸሽ ዘንድ የመማፀኛ ከተሞች እንዲሆኑላችሁ ከተሞችን ለእናንት ለዩ።ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹም ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። የምትሰጡአቸውም ስድስቱ ከተሞች የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞች ትሰጣላችሁ፥ በከነዓንም ምድር ሦስት ከተሞች ትሰጣላችሁ፤ የመማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ። በስሕተት ነፍስ የገደለ ይሸሽበት ዘንድ እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸው ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ።"ዘኁልቅ 35:14
°°ከልቡ ወጥኖ ነፍስ ላጠፉው ለቃየል ያገኝው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት ያደረገለት ቅዱስ እግዚአብሔር ዳግመኛ ከልብ ላልሆነ ጥፋታቸው ባለማወቅ ለሠሩት ስህተታቸው በምድር ሕግ ምትን እንዳይሞቱ ደግሞ ከለላ የሚሆናቸውን ከልብ ስላልተደረገ በደላቸው የሚማጸኑበትን ከተማ ሠራላቸው።
°° ምሕረቱ ከመዓቱ፤ትእግስቱ ከቁጣው ይበልጣል ፍርዱ ልብን የሚያርድ፤መዓቱ መሸሻ የሌለው፤ቁጣው ሥጋን ምድርን የሚያንቀጠቅጥ አምላክ ሆኖ ሳለ አብዝቶ ይታገሳል። ምንማጸንበትን እድሜ ወደ ኋላ ዞረን የሰራነውን በደል የምንሽርበትን የመማጸኛ ጊዜ ይቸረናል።
°°የመማጸኛ ሀገር፤ፍዳ ማቅለያ ሀገር፤የንሰሐ እድሜን መጠቀምያ ሀገር ማግኝት መታደል ነው። ዓለም ባለማወቅ ለተሠራ ጥፋት ፍርድ አታቀልም በከሳሽ ቃል የጸና ቅጣት ታመጣለች። የመማጸኛ ጊዜ የላትም። ይህች እስራኤላውያን የሚጽናኑባት ከበደላቸው አርፈው የሚማጸኑባትን ከተማ ምነው በሰጠን? ብለን አናዝንም ይልቁንስ ቤተክርስቲያን ይህችን መማጸኛ ከተማ ትመስላለች እንገዶች መጻተኞች በደለኞች የሚጽናኑባት በምድር ያለች ሰማያዊት ሀገር እርሷ ናት። በእርሷ እቅፍ ውስጥ ስንት መዓቶች ያልፋሉ ስንት መገፋቶች ይቀላሉ ወደ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት የሚደረገው ሩጫ በእርሷ ዘንድ ነው።
መጽናኛ መማጸኛ ሀገራችን ለኛስ ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት። ሰፊ የምሕረት በር የተተከለባት ስለ በደላችን ፈንታ ቸርነት የምታስገኝልን ከዓለም ሹማምንት ፍርድ አረፍ ብለን እግዚአብሔርን የምንማጸንባት በብዙ ጉድለታችን የምንኖርባት። በማውቅ አብዝተን ለበደልነው ባለማወቅ ላጠፋነው ሁሉ መጠጊያ መማጸኛ ሀገራችን እርሷ ናት።
ሀገረ ምስካይ፤ምስካየ ኅዙናን ቅድስት ቤተክርስቲያን
የተቸገሩ መጠግያ የመጸናኛ ሀገራችን ቤተክርስቲያን።
ዲ/ን ሞገስ አብርሃም
በዓለ ጥምቀት ቃና ዘገሊላ