ዓባይ ባንክ ከራክሲዮ ኢትዮጵያ የዳታ ማዕከል ድርጅት ጋር የሥራ አጋርነት ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የዓባይ ባንክ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዋና መኮንን አቶ ኤልያስ ብርሃኑ እና የራክሲዮ ኢትዮጵያ የዳታ ማዕከል ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጎል ጎሳዬ ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማ ሥነ - ሥርዓቱ ላይ አቶ ኤልያስ እንደተናገሩት ስምምነቱ ዓባይ ባንክ ዘመኑ የደረሰበትን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ግብአት በመጠቀም እጅግ ቀልጣፋ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ የደንበኞች መረጃ ማከማቻ እና ማቀነባበሪያ ማዕከል እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ ደጎል ጎሳዬ በበኩላቸው የሥራ ስምምነቱ ከዓባይ ባንከ ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር አብሮ የሚጓዝ መሆኑን በመጥቀስ፣ በዘላቂነት ዓለምአቀፍ ጥራትና አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ የዳታ ማከማቻ እና ማቀነባበሪያ አገልግሎት መስጠት የሚስችል መሆኑን አውስተዋል፡፡
ራክሲዮ ዳታ ማዕከል ድርጅት በ7 አገራት ገለልተኛ ዳታ ማዕከሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዓባይ ባንክ ዘመኑ የደረሰበትን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በግብአትነት በመጠቀም ለደንበኞቹ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!