እንኳን ደስ አለን!
አስደሳች ዜና ከዓባይ!
ዓባይ ባንክ የPayment Card Industry Data Security Standard (PCI DSS) ከፍተኛ እውቅና የምስክር ወረቀት በማግኘቱ የተሰማንን ታላቅ ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ይህ ከPayment Card Industry Council የተገኘው ልዩ እውቅና ባንካችን የደንበኞቹን የክፍያ ካርድ መረጃ ደህንነትን በአስተማማኝ ደረጃ የሚጠብቅ አሰራር እንዳለው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ነው፡፡
ባንካችን በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉትን ከፍተኛ የመረጃ ደህንነት መጠበቂያ ደረጃዎችን በማሟላት የውድ ደንበኞቹን የክፍያ ካርድ መረጃዎች ሚስጥራዊነት በከፍተኛ ጥንቃቄ የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
ባንካችን በቀጣይም ውድ ደንበኞቹ የሚፈጽሟቸውን የክፍያ ልውውጦች ደህንነታቸው የተጠበቁ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አሰራሮችን በማጠናከር በትጋት ይሰራል፡፡
በተጨማሪ ባንካችን በቅርቡ ለውድ ደንበኞቹ ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን መፈፀም የሚስችላቸውን ቪዛ ኢንተርናሽናል ካርድን እንደሚያቀርብ በዚሁ አጋጣሚ ስንገልጽ ታላቅ ደስታ ይሰማናል፡፡
የጉዞአችን አካል ስለሆኑ ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን!
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ!