Репост из: 📝የአልፋሩቅ መድረሳ ደርሶች በፅሁፍ የሚለቀቅበት ቻናል📝
🔦ተከታታይ አጫጭር ግጥሞች
ክፍል 3
የአለም ፈጣሪ ሀያሉ ጌታችን
አላማ አስይዞ ነው ሲፈጥር ሰዎችን
ጅኖችም ሳይቀሩ ብሎም መላኢካ
ትልቅ ግብ አለበት ነገሩ ሲለካ
በውብ አረበኛ ግልፅ በሆነ ቃል
አላማው ምን እንደሁ ጀሊሉ ነግሮናል
አላህን ልናመልክ አድርገን ብቸኛ
ልንገናኘው ነው ንፁህ ሆነን እኛ
የተጠየቅህ ለት ጌታህ ማን ነው ተብሎ
እንዳትደናገር ዲንን ተማር ቶሎ
ከገባህ አላማው የተፈጠርክበት
ዛሬ ነገ አትበል በፍጥነት ስራበት
ፍሬማ ጥያቄ ሰዎች ሲጠይቁህ
ወደዚች ምድር ለምን መጣህ ሲሉህ
መልስ እንዳትሰጣቸው
ልበላ ልጠጣ ልዝናና ነው ብለህ
ወይም ኖሬ ኖሬ ስጠፋ ልጠፋ
ብለህ እንዳትመልስ የመልስ ቀፋፋ
አእምሮህን ሸቅል ወኔህን አበርታ
ዲንን ለማወቅ ጣር ጠዋትና ማታ
ራስክን ነፃ አውጣ ከጨለማው አለም
ለሰው ልጅ እንደ ዕውቀት ትልቅ ብርሃን የለም
📝 ከአል-ፋሩቅ መድረሳ የተዘጋጀች
አጠር ያለች ግጥም ናት ይቀጥላል...
ኢንሻ አላህ
https://t.me/shortnot_bymedresetulfaruk
ክፍል 3
የአለም ፈጣሪ ሀያሉ ጌታችን
አላማ አስይዞ ነው ሲፈጥር ሰዎችን
ጅኖችም ሳይቀሩ ብሎም መላኢካ
ትልቅ ግብ አለበት ነገሩ ሲለካ
በውብ አረበኛ ግልፅ በሆነ ቃል
አላማው ምን እንደሁ ጀሊሉ ነግሮናል
አላህን ልናመልክ አድርገን ብቸኛ
ልንገናኘው ነው ንፁህ ሆነን እኛ
የተጠየቅህ ለት ጌታህ ማን ነው ተብሎ
እንዳትደናገር ዲንን ተማር ቶሎ
ከገባህ አላማው የተፈጠርክበት
ዛሬ ነገ አትበል በፍጥነት ስራበት
ፍሬማ ጥያቄ ሰዎች ሲጠይቁህ
ወደዚች ምድር ለምን መጣህ ሲሉህ
መልስ እንዳትሰጣቸው
ልበላ ልጠጣ ልዝናና ነው ብለህ
ወይም ኖሬ ኖሬ ስጠፋ ልጠፋ
ብለህ እንዳትመልስ የመልስ ቀፋፋ
አእምሮህን ሸቅል ወኔህን አበርታ
ዲንን ለማወቅ ጣር ጠዋትና ማታ
ራስክን ነፃ አውጣ ከጨለማው አለም
ለሰው ልጅ እንደ ዕውቀት ትልቅ ብርሃን የለም
📝 ከአል-ፋሩቅ መድረሳ የተዘጋጀች
አጠር ያለች ግጥም ናት ይቀጥላል...
ኢንሻ አላህ
https://t.me/shortnot_bymedresetulfaruk