ትንሽ ረዘም ብልም አንብቡት ይጠቅማቸዋል።
የስኬታማ አመራሮች ስድስት የዉጤት ሚስጥራዊ ባህሪያት ‹‹B.A.S.K.E.T››
===============================
ለአንድ ተቋም የላቀ ውጤታማነት ትልቁን ሚና የሚይዘው አመራሩ ነው፡፡
የአመራሩ ጥንካሬ ወይም ድክመት አንድን ትንሽ ተቋም አይደለም አገርን ያህል ነገር ደካማ ወይም ጠንካራ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ያሉ አመራሮች የሚመሩት ድርጅት አትራፊም ይሁን ትርፋማ ያልሆነ እስከ 40 በመቶ ድረስ ውጤታማነቱን የመወሰን አቅም አላቸው፡፡
አመራሩ የበታች ሰራተኞችን ይቀጥራል፣ ያሰራል፡፡ ድርጅቱ ውጤታማ ባይሆን ተጠያቂው የሚሆነው ስራውን በበላይነት የሚያሰራው ወይም ደግሞ ስራውን የሚሰሩ ሰዎችን የቀጠረው ነው ሊሆን የሚችለው፡፡
ለዚያም ነው አንድ ድርጅት ሲመሰረት አመራሩ ማነው?🤔 ተብሎ በቅድሚያ መለየት ያለበት፡፡
የምንመራው ተቋም የፖለቲካ ፓርቲ ሊሆን ይችላል፣ የእግር ኳስ ክለብ ሊሆን ይችላል፣ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅትም እንዲሁ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አትራፊ የንግድ ድርጅትም ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሉም እንደ ተቋም ግን የተቋቋመበትና ሊያሳኩት የሚፈልጉት ራዕይና ግብ አላቸው፡፡
ተቋምን ተቋም ከሚያሰኙት አንዱ መለያ ባህሪያቸው ሰርቶ ሊያሳካቸው የሚፈልጋቸው ግልፅ አላማዎች መኖራቸው ነው፡፡ እነዚህን ዳር ለማድረስ ነው እንግዲህ የአመራሩ ሚና በዓለም አቀፍ ደረጃ የምርጥ አመራር ባህሪያት ምንድን ናቸው?
አንድ አመራር ብቃት የ‹‹BASKET›› ፅንሰ ሃሳብን ያሟላ መሆን አለበት፡፡ ሁሉም ሰው መሪ መሆን ቢፈልግም መሪ መሆን የሚችሉት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ መሪ መሆን ችለውም የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የሚችሉት አሁንም ጥቂቶች ናቸው፡፡ የእጅግ ውጤታማ ሰዎች አመራሮች አንድ መገለጫዎች ‹‹BASKET›› የተባለውን መስፈርት የሚያሟሉ መሆናቸው ነው፡፡ ‹‹ባስኬት›› ሲባል ቅርጫት ለማለት ተፈልጎ አይደለም😄፡፡ ምህፃረ ቃል ነው፡፡
📌 [BASKET = Behavior + Attitude + Skill + Knowledge + Experience + Talent]
1️⃣ B- Behavior…ባህሪ!
Leadership is a potent combination of strategy and behavior. But if you must be without one, be without strategy”
~Norman Skhwarzkopf
እንደሚታወቀው አንድ አመራር ስለሚጠበቅበት የስራ ኃላፊነት ሊወጣው የሚያስችለው ባህሪ ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንዱ መሪ እንኳን ለመምራት ለመመራት የማይሆን ባህሪ ያለው አለ፡፡ እንኳን ሌሎችን ሊመራ ራሱ መሪ የሚያስፈልገው ሰውም አለ፡፡🤥 የመሪነት ባህሪ ራሱን የቻለ ልዩ ገጽታ ነው፡፡ ለዚያም ነው ሁሉም ሰው መሪ መሆን የማይችለው፡፡ ለዚያ ኃላፊነት ዝግጁ የሆነ ባህሪ ሊኖረው ይገባል፡፡ አንድ ሰው በአገራችን ካለው የሊደርሽፕ ተቋምም ሆነ ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ቢማር የመሪነት ባህሪ ካልታደለው ወይም ደግሞ በውስጡ ካላዳበረው ውጤታማ መሪ ሊሆን አይችልም፡፡
መኪና ከፈለግንበት ቦታ ሊያደርሰን የሚችለው ጎማ ሲገጠምለት ነው፡፡ አንድ መሪም እንዲሁ የሚመራውን ተቋም ከዳር ማድረስ የሚችለው ለአመራርነት የሚያበቃ ባህሪ ሲገጠምለት ነው፡፡ ከየትኛውም ተቋም ውጤት በስተጀርባ የአመራሮችን ባህሪ እናገኛለን፡፡ ጥሩ ውጤት ያላቸው ከሆነ ጥሩ የአመራር ባህሪ አላቸው ማለት ሲሆን ውጡቱ ደግሞ ከተጠበቀው በታች ከሆነም ባህሪያቸው የዚያኑ ያህል ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡
አንድ የእግርኳስ አሰልጣኝ ለአሰልጣኝነት የሚሆን ባህሪ ከሌለው ቡድኑ ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ አንድ የፖለቲካ ተቋም /ፓርቲ/ መሪ ፖለቲካዊ መድረክን ወደ ውጤት ለመቀየር የሚያስችል አፈፃፀም ከሌለው በተመሳሳይ መልኩ ፓርቲው እንኳን ምርጫ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ አይደለም የራሱን ህልውና ለማስጠበቅ እንኳን ሊሳነው ይችላል፡፡ አንድ የንግድ ተቋም አመራር ለንግድ አመራርነት የሚያበቃ ባህሪ ከሌለው ድርጅቱ አትራፊ ሆኖ ሊዘልቅ አይችልም፡፡ ይህ የሚያሳየን የአመራር ባህሪ እንደየተቋሙ ባህሪ የሚለያይ መሆኑ ነው፡፡
ለዚያም ነው ታክሲ ሲነዳ የነበረ ሹፌር አውቶብሱን መንዳት የሚሳነው፡፡ 😌
አውቶብሱን ለመንዳት የሚያስችል ባህሪ ከዳበረ ግን በጥሩ ሁኔታ መንዳት ይችላል፡፡ አንድ ቦታ ለውጤት ያበቃ ባህሪ ለሌላም ሊያበቃ የሚችል ሲሆን አንድ ቦታ ላይ ተፈትሾ ያልሰራ ባህሪ ደግሞ በሌላ ቦታ ላይም ሊራ አይችልም፡፡ ሆኖም ለብዙ ተቋማት ውድቀት ትልቁ ምክንያት ያ ተቋም የሚፈልገውን ልዩ የአመራር ባህሪ ካለመኖር ወይም ደግሞ ካለማዳበር የሚመነጭ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚያም ነው አንዳንዴ በአመራር ብቃታቸው ሌላ ቦታ ውጤታማ ሆነው በሌላ ድርጅት ላይ ሲቀጠሩ ድርጅቱን ሊጥሉት የሚችሉት፡፡ ይህም ማለት ባህሪ በየጊዜው የሚዳብር፣ እንደምንመራው ተቋም ባህሪም በአዲስ መልክ የሚሻሻልና ውጤትን የሚወስን አንዱ የመሪዎች ወሳኝ ገፅታ መሆኑን ነው፡፡
2️⃣ A Attitude… አመለካከት
“If your actions inspire others to dream more, learn more, do more and become more, you are a leader”
John Quincy Adams
ይህ የመሪዎች ሌላኛው ውጤት ቀያሪ መገለጫቸው ነው፡፡ የመሪዎች ገንቢ አመለካት ለገንቢ ውጤት የሚያበቃ ኃይል አለው፡፡ አንድ መሪ የድርጅቱን ራዕይ የራሱ ራዕይ አድርጎ ከመነሳት ይጀምራል፡፡ አንዳንድ አመራሮች በአንድ ተቋም ላይ ለመሪነት ሲመረጡ ወይም ደግሞ ሲሾሙ የድርጅቱን ራዕይ ላያውቁት ወይም ደግሞ ላያምኑበት ከቻሉ ግለሰቡና ተቋሙ አልተዋወቁምና ከዚህ መሰል አመራር ውጤት መጠበቅ ማለት ከጠራ ሰማይ ላይ ዝናም ይጥላል ብሎ ጥላ እንደመያዝ ነው የሚቆጠረው፡፡ እንዲሁም የትኛውም የንግድ ተቋም ስራውን የሚገዳደሩት ተወዳዳሪ ተቋማት አሉ፡፡ የንግድ ድርጅትን ብንወስድ ከእነሱ ካልተሻለ ሊጥሉት የሚችሉ ተወዳዳሪዎ አሉት፡፡ በንግድ ውስጥ ያለው አማራጭ፣ ወይም መምራት አልያም መውጣት ነው፡፡ ከፊት መሪዎች ውስጥ አንዱ መሆን መቻል አለበት፡፡ የእግርኳስ ክለብንም ብንወስድ እንዲሁ ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲም ተፎካካሪዎች አሉት፡፡
በመሆኑም የትኛውም ተቋም በአሸናፊነት መንፈስ የተገነባ አመራር ያስፈልገዋል፡፡ ተቋሙ ከሌሎች ተሽሎ የሚገኝ ተቋም እንደሆነና እሱም ያንን በተግባር እውን ማድረግ እንደሚችል የሚያምን፣ ቁርጠኝነቱ ያለው፣ አመራር ያስፈልጋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ራሱንና ተቋሙን አሳንሶ የሚመለከት አመራር እኩል ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡
እንዲሁም የድርጅቱ ውጤት የእኔ ውጤት ነው፤ የድርጅቱ ውድቀት የእኔ ውድቀት ነው ብሎ የሚያምን አመራርም ያስፈልጋል፡፡ የትም ቦታ አንድ መሪ ስራውን ቀይሮ ቢወጣ ለሌላ አመራርነት ሊታጭ የሚችለው ከአሁን ቀደም በመሪነት ደረጃ ያመጣቸው ውጤቶች ታይተው ነው፡፡ የመሪው ህልውና በቀጥታ ከተቋሙ ህልውና ጋር ይያያዛል፡፡ ዛሬ ላይ ለውጤት ያበቃ ባህሪ ነገ ሌላ ቦታ ላይ ይኸው ባህሪ አብሮት ይዘልቃል፡፡ ተቃራኒውም እንዲሁ ነው፡፡ በመሆኑም በአመራርነት ደረጃ ላይ እስከተቀመጠ ድረስ የተቋሙ ውጤት የእኔ ውጤት ውድቀቱም የእኔ ውድቀት ነው ብሎ ማመን መቻል ይኖርበታል፡፡ ይህ እንደ መሪ የሚያስፈልግና ለውጤት የሚያበቃ አመለካከት ነው፡፡
ይቅጥላል....