ልጅ አባቱን እንዲ ይለዋል "አባዬ የሰው ልጅ ዋጋ ስንት ነው?🥹" አባት ገርሞት ሳቅ አለና ከእጁ ላይ ያለውን ሰዓት አውጥቶ አስኪ ይሄን ሰዓት ከሰፈር ጀምረ እስከ ትልቁ የወርቅ መሸጫ ድረስ ስንት ሊገዙህ እንደሚችሉ ጠይቃቸው አለውና ሰጠው ልጅም ያቺን ሰዓት ይዞ ከቤት ወጣ....🚶🏽➡️ ከአንድም የሰፈራቸው ልጆች squad ጎራ አለና እቺን ሰዓት ስንት ትገዙኛላቹ? ብሎ ጠየቃቸው እነሱም አየት አየት አደርጉና 50 ብር ይመቸሃል🙃 አሉት እሱም እምቢ አለና ጉዞውን ቀጠለ.... 🚶🏽➡️ ከሰፈራቸው ካለው የሸቀጥ ሱቅ ሻጭ ጋር ሄደና እሱንም "ስንት ትገዘኛለክ" ብሎ ጠየቀው ደስ ስላለው "500ብር"🤑 ልግዛክ ይለዋል አሁንም ልጁ እምቢ በማለት ይቀበለዉና ሰፈራቸው ካለው አንድ ትንሽ የወርቅ መሸጫ ሱቅ ጎራ ይልና ይሄን ሰዓት ስንት ትገዙኛላቹ ይላችዋል እነሱም ስለወደዱና በጣም መግዛት ስለፈለጉ 2500ብር አንግዛክ ብለው ለመኑ ልጁ አሁንም እምቢ ይልና ጉዞውን ይቀጥላል.... 🚶🏽➡️በስተመጨረሻም ከትልቅ የወርቅና ገጣጌጥ መሸጫ ይገባና ያሳያችዋል እናም ያንን ብራንድ ምርት በማየታቸው ራሱ እየተገረሙ🤩 ሲቀባበሉ ቆይተው ከ10ሺ ብር🤑 በላይ ሰጡት ልጅ ግን ዋጋዉን ለማወቅ እንጂ ለመሸጥ አልነበረምና አሁንም እምቢ ብሎ ይወጣል። በስተመጨረሻ ወደ ቤቱ ይመለሳል ሰዓቱንም ለአባቱ በመመለስ የተፈጠረውን ነገር ሙሉ ይነግረዋል አባትዬውም "አየህ!😊" ይለዋል "የሰውም ውጋ ልክ እንደዚው ነው ሁሉም ዋጋህን የሚወስነው የሱ አቅም እስከሚደርስበት(afford ማድረግ እስከሚችል ደረጃ ነው " አለው
እና የኔ መልእክት 🤌🏾 አንዳንዴ በዙርያችን ያሉት ሰዎች እውነተኛ ማንነትህ ካላወቁና ካልተረዱ ልክ በአስተሳሰባቸው ልክ ላንተ ዋጋ ይሰጡሃል። ይሄን ስል የኛ ዋጋ ሁሌ የማይላስ የማይቀመስ ነው ማለቴ አይደለም ግን ሌሎች ስላሉ ሳይሆን የኛ እውነተኛ ማንነታችን የቱጋ እንዳለ መፈተሽ አይከፋም። ራሳቹን በሚመጥናቹና ነገ ላይ የምትኮሩበት ቦታ ላይ አስቀምጡ
ደና ደሩልኝ 🫰🏽😊
.....✍🏽Abel X