#updates #ተጨማሪ
"የአማራ ታጣቂዎች" ያቋቋሟቸውን አስተዳደሮች ለማፍረስ ከፌደራል መንግስት ጋር ተስማምተናል ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ
ማክሰኞ ሚያዝያ 08 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በምዕራብ ትግራይ በፀለምቲ አካባቢ እና በደቡብ ትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች በአማራ ታጣቂዎች የተቋቋሙትን አስተዳደሮች ለማፍረስ የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲሉ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ ታደሰ ወረደ ገለጹ።
አዲስ ማለዳ ዛሬ ከሰጡት መግለጫ እንደሰማችው “የመጀመሪያው እርምጃ በየአካባቢው የታጠቁ ቡድኖችን ማፍረስ እና የተቋቋሙትን ህገ-መንግስታዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ማፍረስ ነው” ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ፤
"የፍትህ ስርዓቱን ወደነበረበት መመለስ" በተከታይነት ይሰራል ብለዋል።
ጄኔራሉ የታጠቁ ሃይሎች ከፌዴራል ሃይሎች ጋር መጠነኛ ግጭት በመፍጠር ሂደቱን እያስተጓጎሉ መሆናቸውንም አብራርተው የፕሪቶሪያ ስምምነት ግጭት እንዳያገረሽ በሚከላከል መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ እንደገለጹት የፕሪቶሪያ ስምምነት የግዛትን ጨምሮ ሁሉም አለመግባባቶች በህገ መንግስቱ መሰረት መፈታት እንዳለባቸው መደንገጉን አስታውሰዋል።
በራያ አላማጣ አካባቢ የህወሓት ታጣቂዎች ወረራ መፈጸማቸው እየተዘገበ መሆኑን ተከትሎ ነው ይኽ መግለጫ በዛሬው ዕለት መሰጠቱን አዲስ ማለዳ ከክልሉ ቴሌቭዥን ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141