‹‹የሽግግር ፍትህ ልዩ ችሎትን በዚህ ዓመት ስራ ይጀምራል›› ጠቅላይ ፍ/ቤት
ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረቱ በ2017 ሽግግር ፍትህ ልዩ ችሎትን ስራ ለማስጀመር መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ.ም መደበኛ የዳኝነት ስራን ባስጀመሩበት ወቅት ነው፡፡
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ባለፈው አመት የተስተዋሉ ግድፈቶች መኖራቸውን የተቆሙት አቶ ቴዎድሮስ በተያዘው ዓመት ችግሮችን ፈቶ ለመንቀሳቀስ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም በ2017 ዓ.ም በልዩ ትኩረት ተቋማዊ ነፃነትን የጠበቀ የፍትህ ስርዓትን ማጠናከር፣ ለዳኞች ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር፣ የተጠያቂነት ስርዓትን በአግባቡ መተግበር፣ የሽግግር ፍትህ ልዩ ችሎትን ማቋቋምና ሌሎችም የማሻሻያና አዳዲስ አሰራሮች በፍ/ቤቶች ይከወናሉም ነው ያሉት።