"መንግስትም ሆነ ታጣቂ ቡድኖች እኛ ሰላም እንፈልጋለን ይላሉ ሰላምን ማጽናት የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኗባቸዋል"- ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
ሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የቀድሞ የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ታጣቂ ቡድኖች ሰላም እንደሚፈልጉና ተገደው ወደ ትጥቅ ግጭት እንደገቡ ደጋግመው እንደሚያነሱ ገልጸዋል፡፡
ትልቁ ጥያቄ መሆን ያለበት ሰላም እንዴት ይምጣ የሚለው ነው ያሉ ሲሆን መንግስትም ሲጠየቅ ሰላም እፈልጋለሁ፣ ሽማግሌ ልክያለሁ ሞክሬያለሁ፣ ሰላም አጥተናል ሰላም እንዲሆን እመኛለሁ ይላል ታጣቂ ቡድኖችም ሲጠየቁ እኛም ሰላም እንፈልጋለን ተገደን ነው ወደዚህ ነገር ውስጥ የገባነው ማለታቸውን አንስተዋል።
በመሆኑም ሁለቱም ሰላምን እንፈልጋለን የሚሉ ወገኖች ናቸው ሰላምን እንዴት እናጸናለን የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኖብናል ሲሉ ዶ/ር ዳንኤል ገልጸዋል።
በተጨማሪም ይሄ የሰላም ጥያቄ ለመንግሥት እና ለተፋላሚ ወገኖች ብቻ የሚተው መሆን የለበትም ተመሳሳይ የሆነ የግጭት ዓውድ ውስጥ ባለፉ ሃገሮች ልምድ መሰረት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚከተሏቸው ስልታዊ እና ተቋማዊ ሂደቶች አሉ እነዚህም የሃገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትህ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
እነዚህ ሁለት መፍትሄዎች ቀደም ብለው ተጀምረው ተግባራዊ እየሆኑ መሆኑን ተናግረው የተዓማኒነት ጥያቄ ግን እየተነሳባቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ሂደቱ በተቻለ መጠን ሁሉን አሳታፊና ተዓማኒ እንዲሆን ይፈለጋል፤ ነገር ግን በተዓማኒነታቸው ላይ ጥያቄ ምልክት ተነስቶባቸዋል። ይህ አይነቱ የተዓማኒነት ጥያቄ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የተነሳ ጥያቄ አይደለም ተመሳሳይ ሂደት በተከተሉ ሃገሮች በሙሉ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል ብለዋል።
በአማኑኤል ጀንበሩ