ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የ7 መቶ 38 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀች
ማክሰኞ ጥቅምት 26 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛው መደበኛ ስብሰባ የደቡብ ሱዳን የብድር ጥያቄ ተቀብሎ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ 738 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ብድር ስምምት ያጸደቀ ሲሆን ብድሩ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን ለማስተሳሰር የሚረዳ 220 ኪሎ ሜትር ለመንገድ ግንባታ የሚውል መሆኑ ተመላክቷል።
የብድር ስምምነቱ የአምስት አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ10 ዓመት የሚመለስ ሲሆን ብድሩ የሚመለሰው በካሽ ወይም እስከ ፖርት ሱዳን ድረስ በሚቀርብ ድፍድፍ ነዳጅ እንደሆነ ተገልጿል።
የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የሽግግር ህግ አውጪ ምክር ቤት የገንዘብ ስምምነቱን በሰኔ ወር 2016 አጽድቆ የነበረ ሲሆን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር በወቅቱ፤ የመንገድ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል እያደገ ያለውን ትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነት ግንኙነት የሚያሳይና የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የብድር ስምምነት የተፈራረሙት እ.ኤ.አ በግንቦት ወር 2023 ለድንበር ተሸጋሪ መንገድ ግንባታ ይውላል በሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡