ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ገለጸ
ሐሙስ ጥቅምት 28 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ ከህዳር 22 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንደያደርጉ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
አዲሱ መመሪያ ከጥሬ ገንዘብ ንክኪ ነጻ የሆነውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በኢትዮጵያ ለማጎልበት እየተሰራ ያለውን ስራ ለማጠናከር እንደሚያግዝ እና የዲጂታል ግብይትን እየለመደ ያለውን ማህበረሰብ በይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ይህ ኢት ኪውአር ኮድ (EthQR Code) የሚል ሥያሜ የሚኖረው አሠራር ዓለምአቀፍ የአሠራር ልምዶችን መሠረት ያደረገ፣ የክፍያም ሆነ የግብይት ተዋናያንን ሙሉ መረጃ የሚይዝ ነገር ግን ከተወሰኑ አስፈላጊ መረጃዎች በቀር ሌሎቹን በምሥጢር የሚጠብቅ ሥርዓት መሆኑ ተገልጿል።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የዲጂታል ክፍያ አገልግሎትና ግብይት የጥሬ ገንዘብን ዝውውር የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ፣ ሕብረተሰቡ ለሥርቆት፣ በእጁ ያለው ገንዘቡም ለእርጅና እንዳይጋለጥ፤ ከባንክ ውጭ የሚዘዋወር የገንዘብ መጠን እንዲቀንስ፣ ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ገንዘቡን ለማሳተም የሚወጣ ወጪን እንዳይጨምር ለማድረግ ይረዳል ብሏል።