የንግድ ፖሊሲዎች ተደጋግመው መውጣታቸው እና መቀያየራቸው ለስራ አስጊ እየሆነብን ነው ሲሉ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን አሰሙ
ሰኞ ህዳር 02 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የንግድ ፖሊሲዎች ተደጋግሞ መውጣት የንግድ ዘርፉን ስጋት ውስጥ እየጣለው ነው ሲሉ በአስመጪና ላኪ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
በቅርቡ ክልከላ የተጣለበት የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያ እንኳን ብዙ ነጋዴዎችን እና ባለሀብቶችን ችግር ውስጥ እያስገባ ስለመሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ደጋግመው ሲገልጹ ይደመጣል፡፡
እንደነዚህ ያሉት ማሻሻያዎች ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ዓላማ ቢኖራቸውም ፣ ድንገተኛ ትግበራቸው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ መቀልበሳቸው ብዙውን ጊዜ የንግድ ሥራዎችን በአግባቡ እንዳይካሄዱ እየዳረገ ነው ሲሉም ነው ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ያሰሙት ።
ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ አንድ በቡና ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ እንዳሉት በተደጋጋሚ የፖሊሲ ለውጦችን በኢኮኖሚው ላይ መተግበራቸው ለንግድ ድርጅቶች ቀጣይ እርምጃ ከፍተኛ ጥርጣሬን እየፈጠረ ነው ብለዋል።
“ኢኮኖሚው ከመንግስት የፖሊሲ መረጋጋትን ይፈልጋል ምክንያቱም ብዙ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች መወሰን ሚቻለው ያኔ ነው” ያሉት ቅሬታ አቅራቢው ፖሊሲዎች ከመተግበራቸው በፊት በደንብ ሊጠኑ እንደሚገባ አስምረው መንግስትም ከሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት ጋር እንዲወያይ ጠይቀዋል፡
የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አጥላው ዓለሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሚቀያየሩት ፖሊሲዎች የንግድ ባለቤቶች ረጅም ለማቀድ እንዳይችሉና ጥርጣሬ እንዲፈጥርባቸው እንደሚያደርጋቸው ጠቁመዋል፡፡
አክለውም ድርጅቶች በፖሊሲዎች ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦችን በመገመት አሳሳቢ ጉዳዮቻቸውን እና ስራዎቻቸውን በረጅም እቅድ ላይ ከማተኮር ይልቅ በአጭር ጊዜ እቅድና የንግድ እንስቃሴ እንዲገደቡ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የቢዝነስ ተቋማት ፈጣን የፖሊሲ ሽግሽግ የሚያስከትለውን መዘዝ ለመዳሰስ ፈታኝ እየሆነባቸው እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል።