በበጀት እጥረት ምክንያት ያልተጠናቀቁ የመስኖ ስራዎች መኖራቸው ተገለጸ
ማክሰኞ ታህሳስ 01 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ 6ተኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን አኳሂዷል።
በዚህም የመስኖ ፕሮጀክቶች በተያዘው ውል መሠረት ያልተጠናቀቁት በበጀት እጥረት ምክንያት መሆኑን የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
በስብሰባው የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ጨምሮ የአቅም ግንባታ ስራዎች በተገቢው መንገድ ተደራሽ አለመሆናቸው እና የውኃ እጥረት መኖሩ በምክር ቤት አባላት የተነሱ ሀሳብ እና ጥያቄዎች ናቸው፡፡
በጉዳዩም ላይ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትሩ በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የመስኖ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ውል መሠረት ያልተጠናቀቁት በበጀት እጥረት መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ጥራት ያለው የመስኖ አሰራሮችን በመተግበር ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ጉዳዩን ለውሃ፣ መስኖ እና ቆላማ አከባቢ ጉዳይ በተባባሪነት ደግሞ ለከተማ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።