በእስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላቱ ክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው ህመማቸው ብሶባቸዋል ተባለ
ሰኞ ታህሳስ 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ለከፍተኛ ሕመም" መዳረጋቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡
የቅርብ ቤተሰብ እንደሆኑ የተገለጹት እስረኞቹ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ "የማያቋርጥ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው" ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም ሁለቱ ፖለቲከኞች "በተደጋጋሚ አቤቱታ" ከሁለት ሳምንት በፊት ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል፡፡
ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሁለቱ ግለሰቦቹ በሆስፒታል ይቆዩ ቢባልም "ያንን እምቢ ብለው በሰዓታት ልዩነት በማይመች መኪና ጭነው ወደ ማረሚያ ቤት መልሰዋቸዋል" ሲሉ ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አንድ ክርስቲያን ታደለ የቅርብ ቤተሰብ "ቁስሉም አልደረቀም እና ደግሞ ደም እየፈሰሳቸው ነው ሐኪሞቹም ተናግረዋል፤ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም እንደሚችል እና ይህ ሲያጋጥምም እንድታመጧቸው ብለው ነበር ነገር ግን ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ወደ ሆስፒታል አለመወሰዳቸውን" ገልጸዋል፡፡
የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ሰኞ ታህሳስ 7/ 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "ታራሚዎችን ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ ወደሚጠራው ማረሚያ ቤት እንደሚያዘዋውር አስታውቆ ነበር።
ይህን ተከትሎም "በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ" መሆኑን ጠቁሟል።
ኮሚሽኑ በዚሁ መግለጫው ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ የተቋረጠው አገልግሎት ከዛሬ ታህሳስ 14 እንደገና እንደሚጀምር በመግለጫው ገልጾ ነበር።
ነገር ግን የአቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ ቤተሰቦች ዛሬም ምግብ ማስገባት እና እስረኞቹን መጠየቅ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።