የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች አዲስ አበባ ውስጥ መወያየታቸው ተገለፀ
ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የኤርትራ መንግሥትን ለመለወጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ትናንት ውይይት ያካሄዱ ሲሆን ውይይቱም በአዲስ አበባ መደረጉን ተሳታፊዎች መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡
ከሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑ ኤርትራዊያን በዚህ ውይይት መሳተፋቸው የተገለጸ ሲሆን የተደረገውን ውይይት በተመለከተ “የኢትዮጵያ መንግሥት ዕውቅና ሳይኖረው አልሆነም” ሲሉ የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC) ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ የሱፍ አብደላ መናገራቸውን ዶችቬለ ዘግቧል።
ይህንን ውይይት አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ እድሉን እንዴት እንዳግፕኙ የተጠየቁት አቶ የሱፍ አብደላ ይህንን ለማድረግ "እድል ተገኝቷል፣ ያንን እድል ተጠቅመን ውይይቱን አድርገናል" በማለት ማብራሪያ አለመስጠታቸው ተጠቁሟል፡፡
የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ የተባለውና የኤርትራን መንግሥት ለመለወጥ የሚንቀሳቀስ መሆኑን የሚገልፀው ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ የሱፍ አብደላ የፖለቲካ ትግላቸው ማጠንጠኛ የኤርትራ መንግሥት ኤርትራ ውስጥ በሚገኙ አፋሮች ላይ የሚፈጽመው ያሉትን "በደል" እና "ግፍ" ማስቀረት ነው ብለዋል፡፡
"መቼም የኤርትራ መንግሥት ጓደኛ የለውም" ሲሉ የከሰሱት የኤርትራን መንግሥት የሚቃወመው የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ሥራ አሥፈፃሚ አባል አቶ የሱፍ አብደላ፤ የኢሳያስ አፈወርቂን አስተዳደር "ዓለም ላይ ለጎረቤት ሀገሮች ችግር ነው፣ ለራሱ ሕዝብ ችግር የሆነ በአንድ ቡድን የሚመራ መንግሥት ስለሆነ ዛሬ ይህ እድል ተገኝቷል" ማለታቸውን ዘገባው አትቷል፡፡
ይህን ጉዳይ ተከትሎ የኤርትራ መንግሥትም እስካሁን ያለው ነገር እንደሌለ ተመላክቷል፡፡