ከፈትዋ ማህደር
ጥያቄ:– ጠንቋይ አሊያም ደጋሚ ሰው ዘንድ በመሄድ እገሌ ድግምት ተደርጎበታል ወይ? ብሎ መጠየቅ ይቻላልን? የተደገመን ድግምት በሌላ ድግምት ማስፈታት/ማከሸፍስ ይፈቀዳል ወይ?
መልስ:- በፈለስጢን የአልቁድስ ዩኒቨርስቲ የፊቅሂ መምህር የሆኑት ዶ/ር ሑሳሙዲን ኢብን ሙሳ ዐፋነህ እንዲህ ይላሉ:-
አዋቂዎች ወደሚባሉት፣ ጠንቋይ ቤቶችና ወደመሳሰሉት ቤቶች መሄድ በሸሪዓ የተከለከለ ነው። ሙስሊሞች እነርሱ የሚናገሩትንና የሚሉትን ሊያምኑ አይገባም። በሐዲሥ ዉስጥ እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
من أتى عرافاً فسأله عن شيء لم تقبل له صلاة أربعين ليلة
“አዋቂነኝ ባይ ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ አንድን ነገር የጠየቀው ሰው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።” ብለዋል። (ሙስሊም ዘግበውታል)
በሌላ ሰሂህ ሐዲሥም እንደተገለፀው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-
من أتى كاهناً فصدقه فقد كفر بما أنزل على محمد
“ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ የሚለውን ያመነ ሰው በሙሐመድ ላይ በወረደው ነገር ክዷል።” የሐዲሥ አጠናቃሪ (ሱነን) ኢማሞች እና ሌሎችም ዘግበውታል።
ድግምትን በድግምት መፍታት አይፈቀድም። ይህም ሲባል አንድን ድግምት ለማክሸፍ ሲባል ሌላ ድግምት መጠቀም ነው። የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ይህንኑ ከልክለዋል – እንዲህ በማለት፡-
ليس منا من تطير أو تطير له أو تكهن أو تكهن له أو سحر أو سحر له
“ገድ ያየ ወይም የታየለት፣ የጠነቆለ ወይም የተጠነቆለለት፣ ድግምት የሠራ ወይም የተሠራለት ከኛ አይደለም።” (ጦበራኒ ዘግበውታል።)
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ድግምትን በድግምት ስለመፍታት ድንጋጌ ተጠይቀው “የሸይጣን ሥራ ነው።” ብለዋል። (ኢማም አሕመድ እና አቡ ዳዉድ ዘግበውታል።)
ድግምትን ለመፍታትና ለማክሸፍ የተፈቀደው መንገድ በተከበረው ቁርኣን እና ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በተፈቀዱና በተረጋገጡ ዱዓኦች ነው። ከነኚህም መካከል ከአልበቀራ ምዕራፍ ኣየት አል-ኩርሲይ እና ሌሎች የቁርኣን ምዕራፎች “ቁል ያ አዩሀል ካፊሩን”፣ “ቁል ሁወላሁ አሐድ”፣ “ቁል አዑዙ ቢረብ አልፈለቅ” እና “ቁል አዑዙ ቢረብ አን-ናስ” ይጠቀሳሉ። እንዲሁም ሌሎች የሚከተሉት አንቀጾችም ሊጠቀሱ ይችላሉ-
وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنْ أَلْقِ عَصَاكَ فَإِذَا هِيَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ* فَوَقَعَ الْحَقُّ وَبَطَلَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ* فَغُلِبُوا هُنَالِكَ وَانقَلَبُوا صَاغِرِينَ
“ወደ ሙሳም፡- ‘በትርህን ጣል’ ስንል ላክን። (ጣላትም) ወዲያውኑም የሚቀጣጥፉትን (ማታለያ) ትውጣለች። እውነቱም ተገለጸ። ይሠሩት የነበሩትም (ድግምት) ተበላሸ። እዚያ ዘንድ ተሸነፉም። ወራዶችም ኾነው ተመለሱ።” (አል-አዕራፍ 7 ፤ 117-119)
እንዲሁም የዩኑስ ምዕራፍ 79-82 ሌላው ነው።
وَقَالَ فِرْعَوْنُ ائْتُونِي بِكُلِّ سَاحِرٍ عَلِيمٍ * فَلَمَّا جَاءَ السَّحَرَةُ قَالَ لَهُم مُّوسَىٰ أَلْقُوا مَا أَنتُم مُّلْقُونَ * فَلَمَّا أَلْقَوْا قَالَ مُوسَىٰ مَا جِئْتُم بِهِ السِّحْرُ إِنَّ اللَّهَ سَيُبْطِلُهُ إِنَّ اللَّهَ لَا يُصْلِحُ عَمَلَ الْمُفْسِدِينَ* وَيُحِقُّ اللَّهُ الْحَقَّ بِكَلِمَاتِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُجْرِمُونَ
“ፈርዖንም፡- ‘ዐዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ’ አለ። ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ሙሳ ለእነርሱ፡- ‘እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ’ አላቸው። (ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ ሙሳ አለ፡- ‘ያ በርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው። አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል። አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና። አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡”
እንዲሁም የጣሃ ምዕራፍ 65-69
قَالُوا يَا مُوسَىٰ إِمَّا أَن تُلْقِيَ وَإِمَّا أَن نَّكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَلْقَىٰ* قَالَ بَلْ أَلْقُوا فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ * فَأَوْجَسَ فِي نَفْسِهِ خِيفَةً مُّوسَىٰ قُلْنَا لَا تَخَفْ إِنَّكَ أَنتَ الْأَعْلَىٰ * وَأَلْقِ مَا فِي يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوا إِنَّمَا صَنَعُوا كَيْدُ سَاحِرٍ وَلَا يُفْلِحُ السَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ
“ሙሳ ሆይ! ወይ ትጥላለህ ወይም በመጀመሪያ የምንጥል እንኾናለን” (ምረጥ) አሉ። “ይደለም ጣሉ” አላቸው። ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ (እባቦች) ኾነው ወደርሱ ተመለሱ። ሙሳም በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ። “አትፍራ አንተ የበላዩ አንተ ነህና” አልነው። “በቀኝ እጅህ ያለቸውንም በትር ጣል። ያንን የሠሩትን ትውጣለችና። ያ የሠሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ነውና። ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም” (አልን)።”
ድግምትን ለማከም/ለማክሸፍ በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከተላለፉ ዱዓኦች ዉስጥ ደግሞ፡-
اللهم رب الناس أذهب البأس واشف أنت الشافي لا شفاء إلا شفاؤك شفاء لا يغادر سقماً
“አሏሁማ ረቢ ናስ አዝሂብ አልበእሰ፣ ወሽፊ አንተ ሻፊ፣ ላ ሺፋአ ኢል-ላ ሺፋኡከ፣ ሺፋአን ላ ዩጋዲሩ ሰቀማ” የሚለው ይገኝበታል።
ትርጉሙ፡- “የሰው ልጆች ጌታ የሆንክ አላህ ሆይ! መከራን አስወግድ፣ አንተ ፈዋሽ ነህና ፈውስ። ካንተ ፈውስ ዉጭ ሌላ ፈውስ የለም። በሽታን የማያስቀር የሆነ ፈውስን ፈውስ።”
ሌላው ደግሞ መልኣኩ ጂብሪል (ዐ.ሰ) ነቢዩን ካከመበት ዱዓእ መካከል ይኸኛው ይጠቀሳል፡-
بسم الله أرقيك من كل شيء يؤذيك ، ومن شر كل نفس أو عين حاسد الله يشفيك ، باسم الله أرقيك
“በአላህ ሥም አክምሃለሁ፣ ከሚያስቸግርህ ነገር ሁሉ፣ ከመጥፎ ነፍስ ሁሉ እንዲሁም ከምቀኛ ሁሉ አላህ ይፈውስህ። በአላህ ሥም አክምሃለሁ።”
ይህንኑ ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ማለትና ሌሎችንም ዱዓኦችና ዚክሮች መጠቀም ያስፈልጋል። አላህ እጅግ አዋቂ ነው።
https://t.me/alanisquranacademy