ከፈትዋ ማህደር ጥያቄ፡- ወደ አንዳንድ “ሽኽ” ነኝ ወደሚሉ በተለምዶ ኪታብ ገላጭ ወደሚባሉ ሠዎች መሄድ እንዴት ይታያል? አንዲት ሴት ፆመኛና ሰጋጅ ልትሆን ትችል ይሆናል ነገርግን ቤትዋን የዘረፉ ሠዎችን ማንነት ለማወቅ ወደነዚህ “ሸኾች” ትሄዳለች ይህ ነገር እንዴት ይታያል?
መልስ፡- በአሏህ ስም እጅግ አዛኝ እጅግ ሩህሩህ በሆነው።
ማንም ሰው ቢሆን ሩቅን የሚያውቅ የለም። ሩቅን አውቃለሁ የሚል ካለ የጠንቋዮች ምድብ ውስጥ ይካተታል። ጥንቆላን ደግሞ ኢስላም እንደ ክህደት (ኩፍር) ይመለከተዋል። ጠንቋዮች አንዳችን ሩቅ ሊያውቁ ከቻሉ የሚያውቁትን ያወቁት በጂኒዎች አማካኝነት ነው። ከዚያች ጋር ቅጥፈታቸውን ይደራርባሉ።
ሙስሊም ከእነዚህ ሰዎች ደጃፍ መቅረብ የለበትም። በሸኸ አብዱረህማን ኢብኑ ናስር በራክ (የኢማም ሙሀመድ ኢብኑ ሱዑድ ዩንቨርሲቲ የትምህርት ክፍል አባል) እንዲህ ይላሉ፡- “የሙስሊሞች እምነት ውስጥ ከተረጋገጡ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከአላህ (ሱ.ወ) ውጭ ሩቅን የሚያውቅ አለመኖሩ ነው። አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
قُل لَّا يَعْلَمُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الْغَيْبَ إِلَّا اللَّهُ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ
“በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም። ግን አላህ (ያውቀዋል)። መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም በላቸው።” (አን-ነምል 27፤65)
የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንኳን ሩቅን አውቃለው ከማለት ተቆጥበዋል። “እኔ ሩቅን አላውቅም!” ሲሉም ተደምጠዋል። አሏህ አንዲህ ይላል፡-
قُل لَّا أَقُولُ لَكُمْ عِندِي خَزَائِنُ اللَّهِ وَلَا أَعْلَمُ الْغَيْبَ وَلَا أَقُولُ لَكُمْ إِنِّي مَلَكٌ
“ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም። ሩቅንም አላውቅም። ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም።” (አል-አንአም 6፤50)
ሩቅን አውቃለሁ የሚል ተሟጋች ካለ ሙስሊም አይደለም። ይሁንና ድግምተኞችና ጠንቋዮች ሩቅን እናውቃለን በሚል ይሞግታሉ። በእርግጥ አንዳንድ ነገሮችን ሊያውቁ ቢችሉም ብዙ ነገሮችን ግን ይስታሉ። በሀዲስ ውስጥ እንደተዘገበው ጠንቋዮች አንዳንድ ዘገባዎችን የሚቀበሉት የሰማይን ዜና ከሚያዳምጡ አጋንንት /ጅኖች/ ናቸው። እነርሱ የሚሰሟትም በመላኢካዎች ችቦ ከመመታታቸው በፊት የሰሟትን ነው። እዚሁ ላይ መቶ ውሽቶችን በማከል ጠንቋዮች ወደ ደንበኞቻቸው ጆሮ ያደርሳሉ። ደንበኞቻቸው ውሸቶቹን የሚያምኗቸው በእነዚህ ጥራዝ በሆኑ እውነቶች ሳቢያ ነው።
በጥቅሉ ወደ ጠንቋዮች መሄድ ክልክል ነው። በድብቅ የተሰረቀ ነገር የት እንዳለ አውቃለሁ ወደሚል ጠንቋይ ጋር ስለሚሄድ ሲናገሩ መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- “ጠንቋይ ጋር የመጣና የሚናገረውን ያመነ በሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ በወረደው የካደ ነው።”
እነዚህን የመሰሉ ሠዎች “ሸኽ” የሚለው ተቀፅላ አይገባቸውም። “ዓሊም”፣ “ኪታብ ገላጭ”… በሚሉ ሥያሜዎችም ሊጠሩ አይገባም። ሩቅን እናውቃለን የሚል ሰው አታላይ ነው። ሠዎች ሊርቁት ይገባል። ማንነታቸውን የተረዳ ሠውም ያጋልጣቸው። ሰዎችን ከዙሪያቸው ማራቅ ይገባል። ጥንቆላ አላህ (ሰ.ዐ) ዘንድ ውግዝ ከሆኑ ነገሮች መሀል ከዋናዎቹ ይቆጠራል። ወደ ጠንቋይ መሄድም እንዲሁ። አሏህ የተሻለ ያውቃል
https://t.me/alanisquranacademy