ታላቁ የረመዳን ወር እየተቃረበ ነው የረመዳን ወር ሙስሊሞች በጉጉት የሚጠብቁት ታላቅ ወር ነው፡፡ ረመዳን ለአጠቃላይ ማንነታችን ነፍስን ለማስተካከልና ለማረቅ ውድ የለውጥ አጋጣሚም ነው፡፡ ይህ የተላቀ ወር የለውጥ ክፍሉ በፆም ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኝ እውነተኛ የአላህ ፍራቻን ያጎናፃፋል፡፡ሙስሊሞች ከፆሙና ከያዘው ሀይማኖታዊ ፋይዳ አንፃር የመንፈሳዊና የስነምግባር ከፍታ የሚገኝበት ወር እያሉ ይሰይሙታል፡፡
የለውጥ ክፍሎቹ ከሁኔታ ወደ ሁኔታ፣ ከግለሰብ ወደ ግለሰብ፣ከቦታ ወደ ቦታ፣ ከባህሪ ወደ ባህሪ ልዩነት ሲኖረው በአጠቃላይ ሙሉ የለውጥ ክፍሎችን ይዳስስልናል፡፡
👉ሙስሊም ከፈጣሪው ጋር ያለው ግንኙነት
በዚህ የተቀደሰ ወር አንድ ባሪያ ከፈጣሪው አላህ ጋር የሚኖረው ግንኙነት እጅግ ከፍ ብሎና ልቆ እናገኘዋለን፡፡ ይህ ቀረቤታ በዚህ ወርም ሆነ በተቀሩት ወራትም የሚቀጥልና ግዴታ ነው፡፡ የረመዳን ጌታ የተቀሩት ወራትም ጌታ ነውና፡፡ የአላህን ትእዛዛትን መፈፀም ሆነ ከእርሱ ጋር ያለውን ቀረቤታ ለአንድ ወር ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ይህ የለውጥ መንገድ ቀጣይነት ያለውና ዘወትር ትእዛዝን በመፈፀም የታጀበ ነው፡፡ይህ ጉዞ ዘውታሪነትን አንዲላበስና እስከእለተ ፍፃሜ መቃረቢያ እንዲሰነብት ደረጃ በደረጃ የሚያበቃው ነው፡፡
فعن عائشة – رضي الله عنها – أنها قالت: سئل النبي – صلى الله عليه وسلم -: أي الأعمال أحب إلى الله؟
قال: ((أدومُها وإن قل))
አዒሻ(ረዐ) በዘገበችው ሀዲስ ላይ እንዲህ ትላለች፡፡ መልእክተኛው(ሰዐወ) ተጠየቁ፡ የትኛው ስራ ነው ወደ አላህ የተወደደ ? እንዲህ ሲሉ መለሱ፡ (ዘውታሪ የሆነው…ትንሽ እንኳ ቢሆን!)
https://t.me/alanisquranacademy