አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 ዓ.ም የአዲስ የተማሪዎች ቅበላ አሰራርን በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ዩኒቨርስቲው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ እና ልዩ ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል በዚሁ መግለጫ አስታውቋል። አዲስ ይተገበራል በተባለው የቅበላ አሰራር በ2014፤ 2015 እና 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች የሚወጣውን መስፈርት ታሳቢ አድርገው በዩኒቨርሲቲው ፖርታል https://portal.aau.edu.et መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን 50 በመቶ በላይ ማምጣት እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ ግን የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ባገናዘበ መልኩ 60 ወይም 70 በመቶ ድረስ ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል። በመቀጠልም ዩኒቨርስቲው በራሱ የሚያዘጋጀው የመግቢያ ፈተና (Undergraduate Admission Test) የሚኖረው ሲሆን ይህንን ፈተና ማለፍም ሌላው ዩኒቨርሲቲው ያስቀመጠው መስፈርት ነው ። የአፕቲቲውድ (Aptitude) መልክ የሚኖረው እንደሆነ ጠቅሰው የተማሪዎችን የቋንቋ፤ የማመዛዘን እንዲሁም የቀመር አቅማቸውን የሚለካ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ፈተናው ከሌሎች የመግቢያ ፈተና ጋር ተመሳሳይነት ሊኖረው እንደሚችል ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ሆኖም የሚወጣው ፈተና ሙሉ በሙሉ የዩኒቨርስቲው እንደሚሆን አስረድተዋል።ይህን በተመለከተ የተቀመጠ ኮታ እንደሌለ የገለጹት ዶ/ር ሳሙኤል እንደ እቅዳቸው ግን 50 በመቶ በመንግስት 50% በግል ወጪያቸው የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች ለመቀበል እንደሆነ ገልጸው ካልሆነም ቁጥሩ በተወሰነ መልኩ ልዩነት ሊኖረው እንደሚችልም ጠቁመዋል።
@alluexams