ግብፅን ያሳበደው የኢትዮጵያ ከሞሮኮ ጋር የተደረገ ድንቅ ወታደራዊ ስምምነት..🇪🇹👌
ግብፅን ለምን አስደነገጠ ? ኢትዮጵያ ለምን ሞሮኮ ሄደች? ሞሮኮስ ለምን ኢትዮጵያን መረጠች ? የሚለውን የኢትዮጵያን ብዙዎችን ያስገረመ የጂኦ-ፖለቲካዊ ድል አጠር ባለ መልኩ እንመልከት ።
ግብፅ ከስልጣን አልባው የበናዲሩ ሞቃዲሾ መሪ ሀሰን ሼይክ መሀመድ ጋር ያደረገችው የወታራዊ ስምምነት ብዙ የተወራለት ነገር ግን ሁለቱንም መንግስታት ባላሰቡት መንገድ ቅርቃር ውስጥ የከተተ ሆኖ መጥቷል።
ግብፅና ሞቃዲሾ ከተፈራረሙት የጦር ስምምነት እንደሚታወቀው በቀጥታ ኢትዮጵያን ለናጥቃትና ወደ ኤደንና ቀይ ባህር እንዳትወጣ ያለመ ነው። ታዲያ ከስምምነታቸው አንዱ የሆነው ኢትዮጵያን በባህር የምታደርጋቸውን ከንግድ እስከ የባህር ሀይሏ የሚኖሩትን እንቅስቃሴዎች... ግብፅ የአለማችን ወሳች የመርከቦች መተላለፊያ የሆነውን የሲዊዝ ቦይን ኢትዮጵያ ላይ በመዝጋት ፣ ሞቃዲሾ የኢትዮጵያ መርከቦች ወደ ጅቡቲና በርበራ እንዳያልፉ በማገት ኢትዮጵያ ከምግብ እስከ ጦር መሳሪያ ወደ ሀገሯ እንዳታስገባ በመከርቸም ማስገደድ ነው። ( በመሀል ኤርትራም ያለች ሲሆን ለግዜው እንዝለላት)
ታዲያ ይህችን የ129ሚሊየን ህዝብ እናት የሆነች ታላቅ ሀገር ወደ ባህር እንዳትወጣ የተሸረበው ሴራ ሳያንስ እህልና ነዳጅ እንኳን እንዳታስገባ የተሸረበውን ቀመር የተረዳችው ኢትዮጵያ በቀጥታ ያመራችው ቀድማ ወደ አዘጋጀቻት የሰሜን አፍሪካ ወደጅ ሀገር ሞሮኮ (አል-መግሪቢ) ጋር ነበር።
ሞሮኮ በአለማችን ላይ ስትራተጂካዊ የጂኦፖለቲክስ አቀማመጥ ላይ ከሚገኙ ሀገራት አንዷ ነች ። ሞሮኮ በአጭሩ ለማስረዳት ሌሎች አህጉርና ሀገራትን ትተን ወደ ግብፅ የሚሄዱ አብዛኛው መርከቦች መተላለፊያ የሆነው Strait of Gibraltar የባህር ወሽመጥ ባለቤት ነች ።
በዚህም የተነሳ ግብፅ ልክ ኢትዮጵያን በአባይ ምክንያት ታሪካዊ ጠላት እንዳደረገቻት ሁሉ ሞሮኮንም በተመሳሳይ መንገድ በጠላትነት ይዛት ኖራለች። ግብፅ በዚህም የተነሳ ልክ ኤርትራን ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል እንደሰራች ሁሉ የሞሮኮን ተገንጣይ ራሳቸውን ሳህራዊ ሪፐብሊክ ብለው ሚጠሩትን ቡድኖች በመደገፍ ላይ ትገኛለች።
በመሆኑም ኢትዮጵያ በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አማካኝነት ከሌላኛዋ የግብፅ ስትራቴጂካዊ ጠላት ሜዲትራኒያንና አትላንቲክ ውቂያኖስን ከምታገናው ወሳኝ ሀገር ሞሮኮ ሊፐብሊክ ጋር እጅግ ወሳኝ የወታደራዊ ስምምነት ከቀናት በፊት ፈርማለች ። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ከግብፅ ሲዊዝ ካናል ላይ የሚደርስባት የመርከብ መታገት ካለ የግብፅ መርከብ Strait of Gibraltar እንዳያልፍ ይዘጋበታል ማለት ነው። በተመሳሳይ ኢትዮጵያም በኤደን ባህረሰላጤ ላይ አልፎ የሚወጣና የሚገባ የግብፅን መርከቦች ማነቅ ትችላለች።
ይህን ለማድረግ ኢትዮጵያ በቅርብ ኤደን ላይ ከሚሰፍረው ባህር ሀይሏ ባሻገር የመድፍ እርቀት ላይ የሚገኘውን ምድሯንም መጠቀም ትችላለች።
የሞሮኮና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ስምምነት በዚህ ብቻ አያበቃም ምናልባትም ሩቅ ባልሆነ ግዜ ሁለቱም ሀገራት ኢትዮጵያ በሜዲትራኒያን አቅራቢያ በሞሮኮ የናቫል ቤዝ ሊኖራት በተመሳሳይ ሞሮኮም በቀይ ባህር ዙሪያ የወታደር ሰፈር የሚኖራት ይሆናል።
በመጨረሻም ይህ የኢትዮጵያ አስደናቂ የወታደራዊ ዲፕሎማቲክ አካሄድ ሁለት የግብፅ ታሪካዊ ባላንጣ የሞሮኮና ኢትዮጵያ ልዩ አስተማማኝ ጥምረትን የፈጠረ ሲሆን ከፈረሰ መንግስት ጋር ኢትዮጵያ ላይ ያሴረችውን ግብፅን ምትይዝ ምትጨብጠውን አሳጥቷታል።
ይበልጥ ለመገንዘብ ይረዳችሁ ዘንድ
Ahmed Habib Alzarkawi