ኢትዮጵያ ትልቅ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) ካላቸው 5 የአፍሪካ ሀገራት መካከል ተካተተች
አዲስ አበባ፤ መስከረም 24/2017(ኢዜአ)፦በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ኢትዮጵያ ትልቅ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል መካተቷ ተገለጸ።
በዓመቱ ከፍተኛ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) ካስመዘገቡ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ናይጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ግብጽ እና አልጀሪያ ይገኙበታል።
በዚህ መሠረት የአምስቱ ሀገራት አመታዊ ጥቅል ምርት ሲሰላ ወደ 1 ነጥብ 4 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።
ይህ ማለት እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF) መረጃ የአምስቱ ሀገራት አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) ተደምሮ ከቀሪዎቹ የአፍሪካ ሀገራት አመታዊ ጥቅል ምርት ጋር እኩል ይሆናል ነው የተባለው።