የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
****
ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማዕከሉን ጠቅሶ እንዳለው፥ የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።
በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጠይቋል።