የቢቢሲው ጋዜጠኛ አስገራሚ ጥያቄ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
አርባ ሺህ ንፁሐን በሃማ ከተማ በሃፊዝ አል አሰድ በግፍ እየተሞሸለቁ ከመሬቱ ተጣሉ። ጀናዛቸው ተቃጥሎ አመዱ ይደፋ ዘንድ ተፈረደባቸው። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ በልጁ የቀብር ጉርጓዳቸው ተማሰላቸው። አስራ ሶስት ሚሊዮን ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ተፈናቀሉ። በኬሚካልና በፈንጂ በርሜል ነደዱ። ስደተኛ ካምፕ ውስጥ የተጠለሉ ደካሞች እንኳ አልቀሯቸውም ከሰማይ ከምድሩ በቦምብ እየደበደቡ ዕለት ተዕለታቸውን በሰቀቀን ሰቆቃ አኖሯቸው። ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች የገቡበት ታጣ። ስለ እጣ ፈንታቸው ከአላህ በስተቀር ማንም የሚያውቅ ጠፋ። የሰይደናያ እስር ቤት በሮቹ ሲከፈቱ ስለ እስር ቤት የተፃፉ ድርሳናት ሁሉ ገፆቻቸው በአንድ ተጨፍልቀው የዚህን እስር ቤት አንድ ምዕራፍ እንኳ እንደማይወጣቸው ዓለም ተገነዘበ።
ከሃምሳ የግፍ ዓመታት በኋላ የሶሪያ አብዮት አሸነፈ። የቤት ባለቤቶቹ ወደየቀያቸው ተመለሱ። ከቤተሰቦቻቸው ጋር ዳግም ወደ ትዝታቸው አቀኑ። ድላቸው እጅግ ምህረትን ከተላበሱ ድሎች አንዱ ሆነ። ለሃምሳ አመታት በመከራዎች እቶን ሲቀጧቸው የነበሩትን ሁሉ ይቅር አሏቸው። መሳርያ ያነሱባቸው እንኳ ሳይቀሩ ኢዝሀቡ ፈአንቱሙ ጡለቃእ እያሉ ሸኟቸው።
ደማስቆ ከመላው አለም በመጡ ዲፕሎማቶች ተጥለቀለቀች። የቴሌቭዥን ቻናሎች ስለእነሱ ለፈፉ። የዜና ማሰራጫዎች ቀዳሚ ሆነው ከፊት ተሰለፉ። ቢቢሲ ከአህመድ አሽ-ሸርዕ ጋር ቃለ ምልልስ አደረገ። አስገራሚ ጥያቄዎችን ይዞ ብቅ አለ። አህመድ በሚሰጠው መልሶቹ ይህ አለም ምን መስማት እንደሚፈልግ ያወቀ ይመስላል። ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ መልስ ለመስጠት እንዳሰበ ያሳብቃል። ሁለት ጥያቄዎች ግን አስገረሙኝ፡-
"ሴቶች እንዲማሩ፣ ሰዎች አልኮል እንዲጠጡ ትፈቅዳላችሁ?" ሲል የቢቢሲው ጋዜጠኛ ጠየቀ።
ስለሶሪያ ሴቶች በህይወት የመኖር መብት ደንታም የሌለው የምዕራቡ ዓለም ስለሶሪያ ሴቶች የመማር መብት ተጨነቀ። አስራ ሶስት አመታት በፈንጂ በርሜል በኬሚካልና በድሮን ሲጨፈጨፉ ድምፁ ያልተሰማው፣ አሥራ ሦስት ዓመታት ልጆቻቸው ታስረው ሲደፈሩ ዝም ጭጭ ያለው፣ አንድም ጉባኤ ያላደረጉት ፌሚኒስቶች ዛሬ ከየተደበቁበት ወጡ። አሳቢ መስለው ብቅ አሉ። የሶሪያ ሴቶች የመማር መብት ይኖራቸው ይሆን?! ሲሉ ጠየቁ።
ውሸታም! ቀጣፊ!
የአፍጋኒስታን ሴቶችን ገድለው ደፍረው ጨፍጭፈው ሲያበቁ ሀገሩን ለቀው ሲወጡ ሴቶች እዚያ ምድር ይበደላሉ የመማር መብታቸው ይከበር ሲሉ በሚዲያቸው የጮኹት ማን ሆኑና?!
440 ቀናት የጋዛ ሴቶች ሲያለቅሱ የተደበቁ፣ እንደ ሰወኛ አዝነው ዱቄት እንኳ ያልላኩ፣ ጦርነቱ ሲያበቃ የጋዛ ሴቶች ሊጠየቅላቸው የሚገቡ መብቶች አሏቸው ሊሉን ይመጣሉ።
"ሰዎች አልኮል እንዲጠጡ ትፈቅዳላችሁ?!"
ገዳያቸው አይኖቻችሁ እያየ ደማቸውን ሲጠጡ የት ነበራችሁ?! ወንዶቻቸው እስር ቤት ውስጥ ሲዋረዱ፣ ሴቶቻቸው ግፍን ከመራራው ሲጎነጩ፣ ልጆች በእንባቸው ሲታነቁ፣ ልጃገረዶች ሲደፈሩ ሰቆቃቸው እንዲሰማ በመስጂድ ድምፅ ማጉያ እያስተጋቡ በስቃያቸው ሲረኩ ከቶ የት ነበራችሁ?!
ለሃምሳ አመታት የፈለጉትን ያደርጓቸው ዘንድ ለገዳዮቻቸው አልተዋችኋቸውምን?! ህዝቡ ባመፀ ጊዜ ወታደሮቻችሁን ልካችሁ የነዳጅ ትቦውን እንዲጠብቁ ሰራዊታችሁን አላሰማራችሁምን?! አሁን ስለሴቶች የመማር መብት ልትጠይቁ እንዴት ብቅ አላችሁ?! ማፈርያ!
➖➖➖➖➖➖
Mahi Mahisho