ጀርመናውያንን ያስጨረሰው ፕሮፖጋንዲስት !
ፕሮፓጋንዳ ሌላ ስም ቢኖረው ያለጥርጥር ከ ጆሴፍ ጎብልስ ውጭ መስፈርቱን የሚያሟላ አንድም ሰው በዚህ አለም ላይ በህይወት አልኖረም።
ጆሴፍ ጎብልስ የሂትለር የልብ ጓደኛ የአዶልፍ ሂትለርን ስም በጀርመናውያን ልብ ውስጥ ለማስገባት ያልቆፈረው ጉድጓድ ያልፈነቀለው ቋጥኝ አልነበረም።
ፕሮፖጋንዲስት ጆሴፍ ጎብልስ በአዶልፍ ሂትለር ተሹሞ ወደ ስልጣን በመጣ ማግስት ዋነኛ ስራው ያደረገው አይሁዳውያን የሆኑ ጋዜጠኞችን የስነጽሁፍ ሰዎችን ከስራ ገበታቸው ማሰናበት እና በአይሁዳውያን የተጻፉ ኢ-ጀርመናውያን የሆኑ መጽሀፍቶችን ድርሰቶችን ሰብስቦ ማቃጠል ነበር። ከዛ ቡሀላም መላው ጀርመናውያን የሚያው የሚሰማው በጎብልስ ተቀነባብሮ የተዘጋጁ ፕሮፓጋንዳዎችን ብቻ ሆነ! ይህም ጀርመናውያን ከውጪው አለም ተገልለው በመንግስታቸው የተጠመቀላቸውን ፕሮፓጋንዳ ብቻ እንዲጋቱ አስገድዷቸዋል።
ይህ ሰው ሁለተኛው የአለም ጦርነት በጀርመን ሽንፈት ሊጠናቀቅ ቀናቶች እየቀሩት እንኳን ጀርመን እያሸነፈችና ድል እያደረገች እንደሆነ ለብዙዎች በመናገር ላለቀለት ጦርነት የጀርመናውያን ወጣቶች ውድ ህይወታቸውን እንዲሰዎ አድርጓል። የናዚ የጦር ጀነራሎች ተበትነው ሲፈረጥጡና ሂትለር ራሱን እስኪያጠፋ ድረስ ከጎኑ ያልተለየ ከፍተኛ አመራር ጆሴፍ ጎብልስ ብቻ ነበር።
በፕሮፖጋንዳው የብዙ ጀርመናውያን ደም የጠጣው ጎብልስ በስተመጨረሻም ስድስት ልጆቹን ባለቤቱን ጭምር መርዞ ወደ ሲኦል ወረደ! ፕሮፓጋንዳ በአገር ላይ የሚያመጣው ፍጅት ቀላል የሚባል አይደለም!