✔️የሚገርም ታሪክ
ጎበዝ የሆነ ይሄንን እንቆቅልሽ ፍቱት
""""""""""""""""""
✅የኃይል መገኛው የት ነው?
⭐️ “Game of Thrones” በተሰኘው ተወዳጅ ተከታታይ ፊልም ላይ፣ ስለኃይል ምንነት የምታብራራ አንድ ቦታ አለች፤
✍️“እንቆቅልሽ ትወዳለህ ጌታዬ?” አለ ቫረስ፡፡ ከወንበሩ ሳብ ብሎ ወደ ቲሪየን አንገቱን እያቀረበ፡፡ ቫረስ ግዙፍ ነው፤ ረጅም ወፍራም፡፡ በአንፃሩ ቲሪየን ድንክ ነው፡፡ ቫረስ ለነገስታቱ አማካሪና የመረጃ ምንጭ ሲሆን ቲሪየን ደግሞ የነገስታቱ ቤተዘመድ ነው (እህቱ ንግስት ናት)፤ አንዳንዴም የእንደራሴነት (hand of the king) ሥልጣን ተሰጦቶት ይሠራል፡፡
✈️✍️“ለምን ጠየከኝ?” አለ ቲሪየን፡፡ “ከእንቆቅልሾቹ አንዱን ልትነግረኝ ነው?” ብሎ በወይን የተሞላ ብርጭቆውን እንደጨበጠ ቫረስን ለመስማት ወንበሩ ላይ ተስተካከለ፡፡
✍️“…ሦስት ኃያላን ሰዎች በአንድ ቤት ውስጥ ተቀምጠዋል…” አለ ቫረስ እንቆቅልሹን ሲጀምር፡፡
✍️…አንዱ ንጉስ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ጳጳስ፤ ሶስተኛው የናጠጠ ሀብታም፡፡ በመካከላቸው ጎራዴ የታጠቀ ወታደር ቆሟል፡፡ ቅጥረ-ነብሰገዳይ የሚሉት አይነት ነው ወታደሩ፡፡ ተራ ወታደር… ፊደል ቆጥሮ የማያውቅ መኻይም ወታደር፡፡ ሶስቱ ኃያላን ሰዎች አንድ በአንድ ትዕዛዝ ሰጡት- ለወታደሩ! “እነዚህን ሁለት ሰዎች ግደላቸው” ብለው፡፡
“እኔ ህጋዊ ገዥህ ነኝ፣ ትዕዛዜን ፈፅም!” አለው ንጉሱ፡፡ ቀጠለ ጳጳሱም “በአማልዕክቶች ሥም አዝዤሃለሁ፣ የምልህን አድርግ” ሲል አዘዘ፡፡ “ትዕዛዜን ከፈፀምክ ይሄ ሁሉ ወርቅ ያንተ ይሆናል” አለው ያ የናጠጠ ሀብታምም…
✅️ ቫረስ ወደ ቲሪየን አተኩሮ እየተመለከተ “አሁን ጥያቄው፣ ከሦስቱ ማን ይድናል? ማንስ ይሞታል?” ሲል እንቆቅልሹን እንዲፈታ ጠየቀው፡፡
ቲሪየን ጥቂት አሰብ አደረገና “እንደ ባለጎራዴው ሰውዬ ማንነትና ፍላጎት ይወሰናል” ሲል መለሰ፡፡
“ብለህ ነው?” አለ ቫረስ… የነገሩን ውስብስብነት ለማስረዳት እየተዘጋጀ፡፡ “ችግሩ ግን ሰውዬው ተራ ሰው ነው… ብዙም የወርቅ ፍላጎት የለውም፡፡ እምነትም የለውም፣ አልተቀባም፡፡ በሌላ በኩል የነገስታትም ደም የለውም፤ ሊነግስ አይችልም፡፡ ያለው ነገር ቢኖር ስለታም ቆርቆሮ ብቻ ነው (ጎራዴውን ለማለት ነው)”
“ታዲያ እኮ የያዘው ስለታም ጎራዴ ሕይወትንና ሞትን ይወስናል! ጎራዴ እስካለ ድረስ ኃይል አለው ማለት ነው… የፈለገውን መወሰን ይችላል”
“እርግጥ ነው፣ ጎራዴው መግደልና አለመግደል ይችላል፡፡ እሱ ላይ አልተሳሳትክም፡፡ ዳሩ ግን የኃይል ምንጭ ጎራዴ ነው ካልን፣ ወታደሮች እያሉ ሰዎች ሁሉ ለንጉስ መገዛታቸው እንግዳ ነገር አይሆንብህም? ሌላው ቀርቶ እጅግ ፈርጣማዎቹ ወታደሮች እንኳን ለጩጬ አልጋ ወራሽ ይገዛሉ… ለምን?”
“ምክንያቱም ንጉሱም ሆነ ጩጬው አልጋ ወራሽ ሌሎች ወታደሮችን መጥራት ስለሚችሉ ነዋ!”
✅ “ስለዚህ እውነተኛ ኃይል ያለው ‹ሌሎች› የተባሉት ወታደሮች ጋር ነው ማለት ነው? ግን ለምን እነሱስ ጎራዴ ታጥቀው ሳለ ሳያመነቱ ይታዘዛሉ?”
ቲሪየን መልስ አልሰጠም፡፡ የቲሪየንን ዝምታ አይቶ ቫረስ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
✅ “አንዳንዶች ‹እውቀት ኃይል ነው› ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ‹ኃይል ከእግዚአብሄር ነው› ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉ ሰዎችም ‹ኃይል› ከህግ ይመነጫል፣ ሲሉ ይመሰክራሉ፡፡ ችግሩ ግን አንዳንድ ጊዜ በህግ ሥልጣን የተሰጠውም፣ በእግዚአብሄር የተቀባውም፣ ምሁር የተባለውም ሰው እንደ አንድ ተራ ሰው ምንም ማድረግ የማይችሉ አቅመ-ቢስ ሆነው ይገኛሉ፡፡” ብሎ ‹ታዲያ አለ የተባለው ኃይል የታለ?› በሚል አኳኋን ቲሪየንን ተመለከተው፡፡
“ድሮም እንቆቅልሽ አይመቸኝም…” አለ ቲሪየን፡፡ ምን ብሎ እንደሚመልስለት ስለጨነቀው፡፡
✔️ቫረስ ፈገግ ብሎ “ኃይል መገኛው፣ ሰዎች አለ ብለው የሚያምኑበት ቦታ ነው፡፡ ነገሩን ሲያስቡት ያስቃል፡፡ ግን እውነት ነው፤ ኃይል የሚኖረው ሰዎች አለ ብለው የሚያስቡበት ቦታ ነው፡፡ ልክ እንደ ጥላ… ግድግዳ ላይ እንደሚታይ የሰው ጥላ፡፡ እጅግ በጣም ኮስማና የሆነ ሰው እንኳን፣ እጅግ ግዙፍ የሆነ ጥላ ሊፈጥር ይችላል”
@Amazing_fact_433