በ2024 በጎግል ላይ በብዛት የተጠየቁ ጥያቄዎች
ጎግል እየተገባደደ ባለው በፈረንጆቹ 2024 ሰዎች በድረ ገጹ ላይ በመግባት በብዛት የጠየቁትን ጥያቄዎች ይፋ አድርጓል።
ጎግል በገጹ ላይ በ2024 በብዛት ከተጠየቁ ጥያቄዎች ውስጥ “ምን ልመልከት (What to watch)” የሚለው የሚያክለው አልተገኘም ብሏል ስታቲስታ ባወጣው መረጃ።
“ምን ልመልከት?” የሚለው ጥያቄ በየወሩ በአማካኝ ከ6.5 ሚሊየን ጊዜ በላይ እንደሚቀርብም ነው ጎግል ያስታወቀው።
“በርሜል ይንከባለላል? (do a barrel roll?)” የሚለው ጥያቄም በየወሩ በአማካይ ከ3.5 ሚሊየን ጊዜ በመጠየቅ ተከታዩን ደረጃ የያዘ ሲሆን፤ “የኔ አይ ፒ ምንድ ነው (what is my ip)?” የሚለው ጥያቄ በተመሳሳይ በየወር በአማካይ እስከ 3.5 ሚሊየን ጊዜ ይጠየቃል ተብሏል።
“በቅርብ ያለ ግሮሰሪ እስከ ስንት ሰዓት ክፍት ነው? (how late is closest grocery store open)” የሚለው ጥያቄም በፈረንጆቹ 2024 በየወሩ በአማካይ እስከ 3.2 ሚሊየን ጊዜ በጎግል ላይ ተጠይቋል ነው የተባለው።
“በአፕል ውስጥ ምን ያክል ካሪ አለ? የሚለው በየወሩ በአማካይ ከ2.5 ሚሊየን ጊዜ ባለይ ተጠይቋል የተባለ ሲሆን፤ “የፋሲካ በዓል መቼ ነው?” የሚለውም በየወሩ በአማካይ ከ2.3 ሚሊየን ጊዜ በላይ ተጠይቋል።
“የእናቶች ቀን መቼ ነው?” በየወሩ በአማካኝ 2 ሚሊየን ጊዜ፣ “አሁን ስንት ሰዓት ነው?” በየወሩ በአማካኝ 1.8 ሚሊየን ጊዜ እንዲሁም “የ2024 ፋሲካ በዓል መቼ ነው?” በየወሩ በአማካኝ 1.7 ሚሊየን ጊዜ ተጠይቀዋል ነው የተባለው።