የሰው ላይብረሪ
ሰውን እንደ መጽሀፍ የሚዋሱበት "Human Library”
👇🏾
ዴንማርክ ኮፐንሃገን
"የሰው ላይብረሪ/ Human Library” ሰዎችን ለሰላሳ ደቂቃዎች የመዋስ እና የማውራት አገልግሎት ይሰጣል:: አገልግሎቱ የተጀመረው ከብዙ አመታቶች በፊት ሲሆን እስካሁን በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ተጠቃሚ አድርጏል
የሰው ላይብረሪ አላማው ሰዎች የፈለጉትን አርእስት እና ውስጣቸው የሚብሰለሰል ጉዳይን ከማያውቋቸው ሰዎች ጋር እንዲያወሩ የሚያስችል ነው:: ሌላው አላማ ደግሞ የሰዎችን የተሳሳተ ግንዛቤ እና ድምዳሜ ማረቅ ነው
አገልግሎቱን የሚሰጡት የሰው መጽሀፍቶቹ "ድሃ": "ስራ ፈት" : "ሰነፍ": "ሱሰኛ" : "የተካደ"....የመሳሰሉ ስያሜዎች የተለጠፈባቸው መለያዎችን ይይዛሉ
በተለጠፈባቸው አርእስት ዙርያ ማውራት የሚፈልግ ተገልጋይ ልክ እንደ መፅሀፍ ይዋሳቸው እና ለ30 ደቂቃዎች አውርቷቸው ይመለሳል
እነዚህን የሰው መፅሀፍትን ያወሩ ሰዎች የውስጣቸውን ተንፍሰው አልያም ደግሞ ከሌሎች ተምረው እና የተሳሳተ ግንዛቤያቸውን አርመው ይመለሳሉ
👇🏾
ሰው ነው ለሰው መድሃኒቱ !!❤️🙌🏼