በኢቲቪ እየተላለፈ ያለው የፍቅር እስከመቃብር ፊልም በፍርድ ቤት እግድ ወጣበት ‼️
የደራሲ ክቡር ዶ/ር ሐዲስ ዓለማየሁ ወራሽ ፍርድ ቤት የነበራቸውን ክርክር መነሻ በማድረግ የደራሲው ስራ የሆነውን ፍቅር እስከ መቃብር የተሰኘ ድርስት 1ኛ ተጠሪ ወደ ፊልም ቀይሮ ለህዝብ ከማሰራጨት ድረጊቱ እንዲታገድ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ በቀረበው አቤቱታ ላይ ይግባኝ ባዮች አስተያየት እንዲያቀርቡ በተሰጠው ትእዛዝ መነሻነት 1ኛ ይግባኝ ባይ መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው አስተያየት እግድ የሚሰጥ ከሆነ ኪሳራ እንደሚደርስባቸው በመዘርዘር እግዱ ሊሰጥ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የቀረበውን ክርክር እና ማስረጃ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ተክታዩን ትእዛዝ ሰጥቷል፡
👉ትእዛዝ
1/ በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ክርክር ተመርምሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ለክርክሩ መነሻ የሆነውና ወደፊልም የተቀየረው ፍቅር እስከ መቃብር የድርሰት ስራ ለህዝብ እይታ የሚሰራጭ ከሆነ የቅጅ መብት አለኝ በሚሉት መልስ ሰጭዋ ላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ሊደርስባቸጡ የሚችል ከመሆኑም በላይ የማይተካ የሞራል ጉዳት ሊደረስባቸው ስለሚችል በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ክርክር ተመርምሮ ውሳኔ ለመስጠት እስከተያዘው ቀጠሮ ማለትም እስከ #ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ወይም ከወዲሁ ትእዛዙ መነሳቱ እስከሚገልጽ ድረስ ወደ ፊልም የተቀየረው ተጠቃሹ የድርሰት ስራ በማናቸውም መንገድ ለህዝብ እይታ እንዳይቀርብ እንዳይሰራጭ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ/ ቁጥር 154 መሰረት ታግዷል፡፡