ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት አስተላልፏል !
ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
ሥርዓቱን ያሸነፍን መሆኑን ከብልግናው ቡድን በኩል ጥፍር ታክል ልቡ የሚጠራጠር ባተሌ ካድሬ ቢኖር የዛሬው ውሎ በህዝብ የተመታ ታሪካዊ ማህተም ሆኖ ይወሰድ። በአብዮቱም በኩል ካሸነፍን የሰነበትን መሆኑን ማመን ያልቻለ አንድ እንኳን ፋኖ ቢኖር የዛሬውን ቀን ድሉን ከህዝብ ጋር ከፍ አድርጎ ያበሰረበት ዕለት አድርጎ ይፃፈው።
ስርዓቱ ተሸንፏል። ለበሰበሰው ቡድኑ ሽታ አፍንጫችን ስንሸፍን አይናችንም በጋቢያችን ሸፍነነው ካልሆነ በስተቀር ሥርዓቱ ተሸንፏል። በትውልዱ የድል ዋንጫና በኛ መካከል የቀረውን ስንዝር እርቀት ለመጓዝ ግን ጉልበታችን ቄጤማ ሁኗል። ከራያ እስከ ጉበያ፣ ከመተማ እስከ ወንበርማ፣ ከምንጃር እስከ አቸፈር ያካለለ ብርቱ እግራችን ስንዝር ለመራመድ ስለምን አቃተው ካልን መልሱ ትግሉ በአንድ መዋቅር ማሰር ስላልቻልን ነው ይሆናል። የቀረን ነገር ቢኖር ሰኞ በአንድ ቁመን ማክሰኞ ዕለት የድሉን ዋንጫ ማንሳት ብቻ ነው። እዚህ ላይ እንበርታ ።
[ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉም]
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ !
አንድ አማራ !!!
አርበኛ ዘመነ ካሴ